የሚጣሉ ማእቀቦች እያንዳንዱ ሩሲያዊ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆን ይኖርበታል ሲሉ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ተናገሩ፡፡ጠቅላይ ሚንስትሯ ሳና ማሪን ለአውሮፓ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፣ ም…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/tzv3lMC92k1mZcp5ZnXQsaTUaK1Imnbpk-NT7-SF5cFfQGGkW33qf0jsl0vkwmzv2RgPrP-fDlT3kjwtOb2N7sRWw7kG8G-OztKBvXYVx1vg81egiHFps4iCcBlz6MGux3xd28Rc913fvnFhtDKB3l4wf-OmDVw2HMNvEqWJvmyzOo5Exl6sA6OMXN8VMO1LtE9cPQM-5UAR3j5CmIb6ORqQVaoZtqLNx7fhbLH-aTgbWSEDjqrRttuc8vZ87xZZuNwDb6Ia50PArrsuZr0Qr4Ns_ZlETMjAO3D5adQVrU2FAkIsjBgu3foan6p2Byn7sd_7CGJzzUO-77iZLXrZVw.jpg

የሚጣሉ ማእቀቦች እያንዳንዱ ሩሲያዊ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆን ይኖርበታል ሲሉ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሯ ሳና ማሪን ለአውሮፓ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፣ ምእራባዊያን ሃገራት የሚጥሏቸው ማእቀቦች የእያንዳንዱን ሩስያዊ ህይወት የሚነኩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡፡

ለዩክሬን የምናደርገውን ድጋፍ መቀጠል አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ፣ በሩስያ ላይ እስካሁን ከተወሰዱ የማእቀብ እርምጃዎች በተጨማሪ ሊጣሉ እንደሚገባም ሞግተዋል፡፡

የእስካሁኑ ማእቀቦች እምብዛም በሩስያዊያን ላይ ተጽእኖ አላሳደሩም ያሉት ሳና ማሪን የሚጣሉ ማእቀቦች በግለሰብ ደረጃ እያንዳንዱን ሩስያዊ የሚጎዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ነዉ ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሯ ለሩስያዊያን የሚሰጡ የቪዛ አገልግሎቶች ቀላል እንዳይሆኑ መደረጉን ማመስገናቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

መስከረም 03 ቀን 2014 ዓ.ም

ለወቅታዊና ታማኝ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናላችንን ይከታተሉን!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply