የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆን ግዴታ ሊሆን ነው።የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆን ከዚህ በፊት በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የነበር ሲሆን አሁን በወጣ አዲስ አዋጅ ግዴ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/tKWIqisgCpCp2SIg_xql8pj78Tuqj92XWezZjW9epAE_yTkKRcBB_wGFcg_-_XWo6Cbb2vaOfIqCgNSLEYtdPQ5oIuMmOwJK_ydg2eR6KGnuv5D40tM8pX85O0mvUw6LlsC9xvfOwlBSQZA57bOdB2Mh26D0kClgiEX_74j2Nm2iLF2CtJw9LZ2mBHOgMFDIqPEXrHRiGP8GxoL4bJ36keoJGBTOtNm4MDmix82GTv29JwVmif7cQEHKV6YsJNQSFI3-kOIMaLk1ueuag-JnmNpeBaAMo8hhlTI_E-YuVfSrzkKYr8ryO_Q0VTEGYWDgEsLZc34pcKldy08DH9EKfg.jpg

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆን ግዴታ ሊሆን ነው።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆን ከዚህ በፊት በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የነበር ሲሆን አሁን በወጣ አዲስ አዋጅ ግዴታ ሆኗል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆን ግዴታነት በፌደራል ደረጃ በሚመሠረተው ምክር ቤት የሚወሰን መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉቀን አርጋው ተናግረዋል።

የጤና ወጪ ከአመት አመት ጭማሪ እያሳየ መሄዱን ያነሱት ዶክተር ሙሉቀን፣ ለአገልግሎቱ ተጠቃሚነት ተገቢ የሆነ ሰው አባል የመሆን ግዴታ አለበት ነው ያሉት።

አባል ለመሆን ማንኛውም ሰው የመመዝገቢያ ክፍያ እና የአባልነት መዋጮ መክፈል እንደሚኖርበት ያነሱት ዶክተር ሙሉቀን፣ እንደየ ደረጃው የገንዘብ መጠኑ የተለያየ መሆኑንም አስረድተዋል።

ለገጠር 375፣ ለገጠር ከተሞች 500፣ ለትልልቅ ከተሞች 665 እና ለአርብቶ አደር አከባቢዎች ደግሞ 325 ብር መሆኑን ገልጸዋል።

መክፈል የሚችል ከሆነ እራሱ እንደሚከፍል እንዲሁም መክፈል የማይችል ህብረተሰብ ግን ተመርጦ ፣ተለይቶ በወረዳ እና በክልል መንግስት ወጪው የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

በዚህም በአመቱ ለጤና መድህን ከከፈሉ ተጠቃሚዎች 3.1 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገልጿል።

የመክፈል አቅም ከሌላቸው እና መንግስት ከሚደጉማቸው ተጠቃሚዎች ደግሞ ከ 712 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከመደበኛው ክፍለ ኢኮኖሚ ውጪ የሚገኙ ከ80 በመቶ በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የያዘ ነው።

በእስከዳር ግርማ

ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply