የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ባህሪን አለማወቅ ብዙዎችን ከዋና ግባቸው አናጥቦ መንጋ እያደረጋቸው ነው፡፡  (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013ዓ.ም)   ከሰሞኑ እንኳን በጀኔራል አበባው ታደሰ እ…

የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ባህሪን አለማወቅ ብዙዎችን ከዋና ግባቸው አናጥቦ መንጋ እያደረጋቸው ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013ዓ.ም) ከሰሞኑ እንኳን በጀኔራል አበባው ታደሰ እ…

የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ባህሪን አለማወቅ ብዙዎችን ከዋና ግባቸው አናጥቦ መንጋ እያደረጋቸው ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013ዓ.ም) ከሰሞኑ እንኳን በጀኔራል አበባው ታደሰ እና ባጫ ደበሌ በተከፈቱ ሀሰተኛ ገፆች እንዲህ አሉ እንዲህ ተባለ እየተባለ ትክክለኛው የህዝብ ሞት ተደብቆ ሰንብቷል፡፡ በምዕራብ ኦሮሚያ ኦነግ ከ50 በላይ አማራዎችን እንደገደለ መረጃዎች ቢወጡም፣ የ 50 ንፅሃን ሞት በጃል ማሮ ተገደለ አልተገደለም በሚል ብሽሽቅ የዜጎች ስቃይ ተዳፍኖ ውሏል፡፡ የሀገሪቱ ውስብስብ ችግር የግለሰቦች መኖር አለመኖር፣መሳሳት እና አለመሳሳት ይመስል በግለሰቦች ዙሪያ መንጋው ሲነታረክ ይውሏል፡፡ ይህ መነታረክ የህዝብን ሞት ያፋጥናል እንጂ መድህን አይሆንም፡፡ በውሸት መረጃ እውነት እየተደበቀ ፣ሰው በአልባሌ መረጃ ተጠምዶ እውነቱን …እየሳተ እንደሚገኝ አንድ የኮሚኒኬሽን ምሁር ለአሻራ ተናግረዋል፡፡ መዳረሻ ግብ እና ሀሳብ አልባ የሌለው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ውሸቱን እያመነ እውነቱን እየጣለ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ እውነተኛ የመረጃ ምንጭን ማጥራት፣ ለምን እና እንዴት ተባለ ብሎ መገመት እንጂ መረጃን ሳያላምጡ መዋጥ ተገቢ እንዳልሆነም ምሁሩ ተናግረዋል፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ የሚለቀቁ መረጃዎች 70% የመረጃ ባለቤታቸው የማይታወቅ እና በደህንነት ሰዎች ሆን ተብለው ለማሳሳት የሚወጡ እንደሆነ ለአሻራ ተናግረዋል፡፡ መረጃን ከምንጩ ማጥራት ተገቢ ነውም ብለዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply