የማህጸን በር ካንሰርን አስቀድሞ ለመከላከል የሚስችል ክትባት ለስድስት ቀናት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በሴቶች ላይ የሚከሰተው የማህጸን በር ካንሰር ብዙዎችን የሚያጠቃና ከእለት እለት ቁጥሩ እየጨመረ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡የአዲሰ አበባ ጤና ቢሮ የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቢዮት ከበደ ለአሐዱ እንደተናገሩት የማህጸን በር ካንሰርን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ክትባት ከታህሳስ 17- 22 ቀን 2013ዓ/ም ድረስ ይሰጣል፡፡

ክትባቱ በሐገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ የተናገሩት የኮምኒኬሽን ዳይሬክተሩ በአዲስ አበባ በ10ሩም ክፍለ ከተማ በጤና ጣቢያዎችና በትምህርት ቤቶች ይሰጣል ብለዋል፡፡እድሚያቸው ከ14 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጅ አገረዶች ክትባቱ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡በትምህርት ቤቶችና በጤና ጣቢያዎች በአጠቃላይ ከ49 ሺ በላይ ልጅ አገረዶችን ተደራሽ ለማድረግ ውጥን መያዙን የተናገሩት አቶ አቢዮት ጤና ቢሮው ክትባቱን ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡

እድሚያቸው ከ14 ዓመት በታች ያሉትም ክትባቱን ቢወስዱ ችግር ባይኖረውም ሐገሪቷ ካላት የምጣኔ ሐብት አቅም አንጻር ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ወላጆችም የማህጸን በር ካንሰር የቅድመ መከላከል ክትባትን ልጆቻቸው እንዲወስዱ ግፊት ማድረግ አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል፡፡

****************************************************************************

ቀን 18/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post የማህጸን በር ካንሰርን አስቀድሞ ለመከላከል የሚስችል ክትባት ለስድስት ቀናት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply