የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ ያከናወኑ ሴቶች ህክምናውን እያገኙ አይደለም ተባለ፡፡የቅድመ ካንሰር ልየታ አከናውነው ምልክቱ የተገኘባቸው ሴቶች የህክምና አገልግቱን እያገኙ አለመሆኑን የነ…

የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ ያከናወኑ ሴቶች ህክምናውን እያገኙ አይደለም ተባለ፡፡

የቅድመ ካንሰር ልየታ አከናውነው ምልክቱ የተገኘባቸው ሴቶች የህክምና አገልግቱን እያገኙ አለመሆኑን የነገሩን በጤና ሚኒስቴር በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፋጻሚ እና የማህጸን በር ካንሰር ፕሮግራም ተጠሪ ወ/ሮ ታከለች ሞገስ ናቸው፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ ካንሰር ልየታውን የሚያከናውኑ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ እና ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሲነጻጸር መሻሻሎች መስተዋላቸው የተገለጸ ሲሆን በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ግን የህክምና አገልግቱን እያገኙ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

የቅድመ ካንሰር ልየታ ግንዛቤ ቢኖርም ህክምናው ላይ ግን የግብዛቤ እጥረቶች መኖራቸው ተነግሯል፡፡
የቅድመ ካንሰር ምልክት ካንሰር ነው ማለት አይደለም ያሉ ሲሆን ምልክቱ ከታየበሚደረግ የህክምና ክትትል እንደሚዳን ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ተብሏል፡፡

የቅድመ ካንሰር ልየታ ህክምና የሚሆነው የተስተዋለውን የቅድመ ካንሰር ምልክትን ወደ ካንሰርነት እንዳይለወጥ ማድረግ መሆኑን ገለጹ ሲሆን ፤ የቅድመ ልየታ ከተከናወነ እና ክትባቶች ከተወሰዱ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰርን መከላከል እንደሚቻል ተነግሯል፡፡
በህክምናው እስከ አንድ ወር ድረስ ከግብረ ስጋ ግንኙነት የመታቀብ ሁኔታ አለ ተብሏል።

በህክምናው ላይ የወንዶች በተለይም የባሎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እገዛ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ 2 ጊዜ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ ካከናወነች 70 በመቶ ተጋላጭነቷን እንደሚቀንስ ተጠቁሟል።

ከ30 ዓመት በላይ የሆነች፣ የግብረስጋ ግንኙነት የጀመረች ሴት በ3 ዓመት አንዴ እንዲሁም ኤች አይቪ ኤድስ በደሟ ውስጥ ካለ በ2 ዓመት አንዴ የቅድመ ካንሰር ልየታ ልታከናውን ይገባል ተብሏል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply