የማሊ ምርጫ እስከ አምስት ዓመት እንዲራዘም ሀሳብ ቀረበ

የወታደራዊ መፈንቀል መንግሥት በተካሄዳባት ማሊ የዴሞክራሲ ምርጫን የሚደረግበትን ምክረ ሀሳብ እንዲያቀርብ የተሰየመው አካል ትናንት ሀሙስ በሰጠው መግለጫ በሚቀጥለው የካቲት ወር ይካሄዳል የተባለው ምርጫ ከ6 ወር እስከ አምስት ዓመታት ለሚደርስ ጊዜ መዛወር የሚችል መሆኑን በመግለጽ ምክረ ሀሳብ ማቅረቡ ተገለጸ፡፡

ወታደራዊ መንግሥቱ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አቡባካር ኢብራሂም ኬታን በመፈንቀለ መንግሥት ካስወገደ በኋላ፣ የሽግግር መንግሥት ሥልጣኑን የወሰዱት ኮሎኔል አሲሚ ጎዮታ ከ18 ወራት ቆይታ በኋላ በሚቀጥለው የካቲት ምርጫ እንደሚደርግ አስታውቀው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ በሰሜን አገሪቱ ክፍል ይንቀሳቀሳሉ በተባሉ የእስልምና ኃይሎች ጥቃት ምክንያት በማድረግ የተባለው የምርጫ ወሬ ሳይሰማ መቆየቱ ተነገሯል፡፡ 

የማሊ መንግሥት ምርጫ የሚደረግበትን ጊዜ አስመልክቶ የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ተቀብሎ የደረሰበትን ውሳኔ በጥር ወር መጨረሻ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

ፈረንሳይ ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል አስገብታው የነበረው በሺዎች የሚቆጠር ጦሯን ከማሊ ስታስወጣ ሩሲያ ደግሞ ወታደራዊ አሰልጣኞችን ወደ ማሊ መላኳ ተሰምቷል፡፡ 

ምዕራባውያኑ ሩሲያ ቀስ በቀስ ወታደራዊ ይዞታዋን እያስፋፋች ትመጣለች የሚል ስጋት ያደረባቸው መሆኑም በሮይተርስ ዘገባ ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply