#የማሕፀን ግድግዳ እጢ፡-የማሕፀን ግድግዳ እጢ በእንግሊዘኛ ዩትራይን ፋይብሮይድስ (Uterine Fibroids) ወይም ማዮማስ (Myomas) ይባላል።የተለያዩ የማህጸን እጢ ክፍሎች ሲኖሩ በ…

#የማሕፀን ግድግዳ እጢ፡-

የማሕፀን ግድግዳ እጢ በእንግሊዘኛ ዩትራይን ፋይብሮይድስ (Uterine Fibroids) ወይም ማዮማስ (Myomas) ይባላል።

የተለያዩ የማህጸን እጢ ክፍሎች ሲኖሩ በብዛት ግን የማህጸን እጢ እየተባል የሚታወቀው የማህጸን ጡንቻ ላይ የሚነሳ በአካባቢያችን ካሉ ነገሮች አንጻር ስንገልጸው ልክ እንደ ድንች የሚፈለፈል ነገር እንደሆነ ዶ/ር ልንገርህ ይናገራሉ፡፡

#ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ የማህጸን እና ጽንስ ሀኪም ናቸው፡፡
የማህጸን እጢ የሚከሰትበት ትክክለኛ ምክንያት ባይታወቅም እንደ መንስኤ የሚነሱት ግን ከታች የተዘረዘሩት እንደሆኑ ባለሙያው ያነሳሉ፡፡
– የወር አበባቸው ቀድሞ የመጣ ሴቶች
– በተጨማሪም በዘር የሚመጣ ተጋላጭነትም አለ ለምሳሌ ጥቁሮችን በሰፊው የማጥቃት
– ብዙ እርግዝና ያልነበራቸው ሴቶች ወይም መኻን ሴቶችም ተጋላጭ ይባላሉ።
– ኤስትሮጅን እና ፕሮጀስትሮን ሆርሞኖች መጠንን በሰውነት ውስጥ ሊጨምሩ የሚችሉ እንደሆኑ ይናገራሉ።
የማህጸን እጢ አብዛኛውን ግዜ አንዲት ሴት መውለድ በምትችልበት የእድሜ ክልል እንደሚከሰት ባለሙያው ያስረዳሉ፡፡

#ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

አብዛኛውን ግዜ ምልክት አልባ ናቸው ይላሉ ባለሙያው
ነገር ግን እድገቱ በጨመረ ቁጥር የሚፈጥራቸው ምልክቶች አሉ ፡፡
– የታችኛው የጀርባ ህመም
– ከእንብርት በታች ህመም
– ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
– የሆድ ድርቀት
– ከእንብርት በታች እብጠት
– የማህጸን ግድግዳን በመግፋት ከፍተኛ የሆነ የወር አበባ ፍሰት እንዲኖር ማድረግ ከምልክቶቹ መሀከል እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡
የማህጸን እጢ በብዛት የወሊድ ችግር አይፈጥርም ግን ከስንት አንዴ እና ባልተለመደ መልኩ መካንነት ሊያጋጥ እንደሚችል ዶ/ር ልንገርህ ያነሳሉ

#ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

ህክምናዎቹ ሚወሰኑት ምን አይነት እጢ ነው በሚለው ነገር ይሆናል ፡፡
ምልክት አልባ የማህጸን እጢ ህክምና ማድረግ አያስፈልገውም፡፡

ነገር ግን የማህጸን እጢው ምልክት ያለው ከሆነ ህክምናዎች አሉት፡፡
-አንደኛው ህክምና የወር አበባ መዛት ካለ የወሊድ መቆጣጠሪያ ይሰጣል፡፡

– ሌላው ደግሞ በቀዶ ህክምና የማህጸን እጢዎችማውጣት (myomectomy)
ይህ አማራጭ በቀዶ ህክምና እጢዎቹን ብቻ ለይቶ ማውጣት እንደሆነ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የማህጸን እጢ ወደ ካንሰር የሚቀየር በሽታ እንዳልሆነ ዶ/ር ልንገርህ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply