
የማኅበረ ቅዱሳን በደሌ ማእከል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ዲ/ን ዳኜ ዘርፉ መታሰሩ ተገለጸ። በበደሌ ወረዳ ማዕከል የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና ሰባኬ ወንጌል መንፈሳዊ መጻሕፍትንም በኦሮሚኛ ቋንቋ በመተርጎም እና በመጻፍ የሚታወቀው አገልጋይ ዲያቆን ዳኜ ዘርፉ እና የቡኖ በደሌ ሃገረ ስብከት አደራጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ቢልልኝ ዘነበ ጥር 25/2015 ዓ.ም ታስረዋል። ወንድም ቢልልኝ ከሁለት ቀናት በፊት ታስሮ የተፈታ ሲሆን ዛሬ በድጋሚ አስረውታል ።
Source: Link to the Post