የማኅበራዊ ሚድያ መዘጋት በመገናኛ ብዙኃን ሥራ ላይ ችግር ፈጥሯል – ባለሞያዎች

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-fa74-08db20db5630_tv_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የጣለው ገደብ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን መረጃ የማሰባሰብ፤ የማደራጀትና ለሕዝብ ተደራሽ የማድረግ መብት ላይ ችግር መፍጠሩን ገለፀ፡፡

የምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታምራት ኃይሉ፣ እርምጃው በተለይም በበይነ መረብ ለሚሰራጩት ሚዲያዎች እንቅፋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ማኅበራዊ ሚድያውን ተጠቅመው የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያቀርቡት አዘጋጆች በበኩላቸው የተጣለው ገደብ ሥራቸው ላይ ጫና መፍጠሩን ይናገራሉ፡፡ በጉዳዩ ዙርያ አስተያየት የተጠየቁ አንድ ባለሞያም በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ ሲሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply