#የማንኮራት ችግርበእንቅልፍ ጊዜ ማንኮራፋት የበርካታ ሰዎች ችግር ሆኖ ይስተዋላል።ምንም እንኳ ለሚያንኮራፋው ሰው ባይታወቀውም በአካባቢው ያለውን ሰው ሰላም መንሳቱ ግን አይቀሬ ነው።ማንኮራፋ…

#የማንኮራት ችግር

በእንቅልፍ ጊዜ ማንኮራፋት የበርካታ ሰዎች ችግር ሆኖ ይስተዋላል።

ምንም እንኳ ለሚያንኮራፋው ሰው ባይታወቀውም በአካባቢው ያለውን ሰው ሰላም መንሳቱ ግን አይቀሬ ነው።

ማንኮራፋት በአለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሰዎችን የሚያጠቃ የተለመደ ችግር ሲሆን በእንቅልፍ ጥራት እና በአጠቃላይ ጤና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከአንገት በላይ ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ብስራት ጌታቸው ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

#ማንኮታፋት ምንድነው ?

ማንኮራፋት የምንለው ብዙ ሰው የሚያውቀው ድምፅ ሲሆን በተለይ ላንቃችን ፣ከአፍንጫ ጀርባ ያሉ ቦተዎች እና አጠቃላይ የላይኛው የመተንፈሻ ቱቦዎች የሆነ ቦታ ላይ ጥበት ሲኖረው ወይም አየር መዛባት እና የተረበሸ አየር በአፍንጫችን ጀምሮ እስከ ላይኛው ድምፅ እስከምናወጣበት ጉሮሯችን ድረስ የሆነ ቦታ ላይ መረበሽ ካለ የሚፈጠር የድምፅ አይነት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

የህፃናቶች ማንኮራፋ እና የአዋቂዎች ማንኮራፋት የሚመሳስላቸው ነገር ቢኖርም ከአመጣጡ እና ከምክንያቱ ጀምሮ ይለያያል ይላሉ ባለሙያው ፡፡

#የህፃናት ማንኮራፋት

የህፃናት ማንኮራፋት በብዛት ከአፍንጫቸው እና ከአፍንጫቸው ጀርባ የሚነሳ ችግር ነው ፡፡

“Adenoidal hypertrophy “ ብዙ ልጆች ላይ ያለ ሲሆን ከአፍንጫ ጀርባ ያለው ስጋ ሲጨምር የሚከሰት ነው በተለይ ከ8 አመት በበታች የሆኑ ህፃናቶች ሁሉ “adenoid” የተባለ ከአፍልጫ ጀርባ ያለ ቶንሲል አላችው ይህ ስጋ በሚያብጥበት ግዜ ከአፍንጫ ጀርባ ያለውን የአየር ቦታ ይዘጋዋል ስለዚህ ልጆች በአፍንጫቸው ለመተንፈስ ይቸገራሉ በዚህ ምክንያት እያንኮራፉ በአፋቸው መተንፈስን ይመርጣሉ ፡፡

#የአዋቂዎች ማንኮራፋት

አዋቂዎች ላይ ያለ ማንኮራፋት ከፊት ለፊት ያለው ከአፍንጫ ጀምሮ እስከ ታችኛው ድምፅ እስከምናወጣበት ጉሮሯችን ድረስ የትኛውም ቦታ ላይ የአየር ቱቦ መጥበብ ካለ የማንኮረፋት ችግር ሊከሰት እንደሚችል ባለሙያው ይናገራሉ ፡፡

ሌላኛው ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ሰዎች በብዛት የማንኮራፋት ችግር ይገጥማ ቸዋል ማክንያቱም ከአፍንጫ ጀርባ እና ከአፍ ጀርባ ያሉት ቦታዎች በብዛት በግራና በቀኝ ያሉ ቦታዎች ከሽፋናቸው ስር ስብ ስለሆነ ያለው የሰውነት መጠን በሚጨምርበት ግዜ ስቡ እየጨመረ ስለሚመጣ ቦታው ይጠባል በዚ ግዜ ደግሞ ማንኮራፋት የማይቀር እንደሆነ ዶ/ር ብስራት ተናገረዋል፡፡

በተጨማሪ የትራስ ችግር ወይም የአተኛኘት ሁኔታም ጊዜያዊ የማንኮራፋት ችግር ሊመጣ ይችላል ይላሉ ፡፡

#ማንኮራፋት የሚያመጣው ችግር

#አዋቂዎች ላይ

-በቂ እንቅልፍ አለማግኘት
-ሰውነት ድባቴ ውስጥ መግባት
-የሆርሞን መዛባት
-አንዳንዴ የልብ ችግሮችን ማምጣት
-አንዳንድ ሰዎች ላይ የጨጓራ ችግር ሲያመጣ በቂ እንቅልፍ ባለማግኘት እና በመጨናነቅ ግፊትም ሊመጣ እንደሚችል ዶ/ር ብስራት ተናረዋል፡፡

#ህፃናቶች ላይ

ህፃናቶች ላይ ማንኮራት የሚያስከትለው ችግር ድምፅ ማውጣታቸው እና ለሊት እንቅልፍ መረበሻቻ ብቻ ሳይሆን የልብ ችግር ያመጣል ፡፡

በሚያንኮራፉበት ግዜ በቂ ኦክስጅን ወደ ሳንባቸው ስለማይገባ ሳንባቸው በቂ ኦክጅን የማይቀበል ከሆነ ወደ ልብ የሚያደርሰውን የኦክስጅን መጠን ይቀንሰዋል ስለዚህ ልብ በቂ ኢክስጅን ስለማያገኝ ለከፍተኛ ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ያስረዳሉ፡፡

#የሚደረጉ ህክምናዎች

የልጆች ማንኮራፋት ብዙ ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ በመታየት በባለሙያው ክብደቱ ታይቶ ሁለት አይነት ህክምናዎች ይሰጣቸዋል ፡፡

-የመድኃኒት የህክምና አማራጭ
-በቀዶ ህክምና እብጠቱን ማሶጣት

አዋቂዎች ላይም በተመሳሳይ ችግሩን ማከም ሲሆን ሌላው በውፍረት የመጣ ከሆነ ውፍረት መቀነስ፣ የትራስ ችግር ከሆነ የሚመቸንን በማድረግ ማስተካከል እንደሚመረጥ ተናግረዋል ፡፡

በመጨረሻም ማንኮራፋት በአብዛኛው መታከም የሚችል ነገር በመሆኑ የማንኮራፋት ችግር ያለባቸው ሰዎች ሀኪም ጋር ሄዶ መታየት እና ተገቢውን ህክምና ማድረግ እንዲሁም ከሀኪም ጋር መመካከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ልጆች ላይ የሚከሰት የማንኮራፋት ችግር በጣም ትልቅ በሽታ በመሆኑ እንደቀላል ሊታይ እንደማይገባ እና ትንሽም የማንኮራፋት ችግር ያለባቸው ልጆች ወደ ሃኪም ሄደው ተገቢውን ክትትል እና ህክምና ማግኘት እንደሚገባ ዶ/ር ብስራት ተናግረዋል፡፡

በሃመረ ፍሬው

መጋቢት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply