
የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ አንድ አጋችን ሰዎችን አስገድዶ ከተቀበለው ገንዘብ ጋር በቁጥጥር ስር አዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አጋች ሁኔ ደጀን ነዋሪነቱ ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ደንብ ከተማ ሲሆን ታጋች ፈጠነ ደጀንን በታች አርማጭሆ ወረዳ ያይራ ቀበሌ ድረስ በመጓዝ ልጁን አግቶ ወደ ጫካ ገብቶ ነበር። በድርድር ላይ ሳለ የታጋች ቤተሰቦች የአጋች መኖርያ ወደሆነው ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት በማመልከታቸው የወረዳው የፀጥታ ሃይሎች ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ከታጋች ቤተሰብ የተቀበለውን ብር በሻንጣ እንደቋጠረ ወደ መኖርያ ቀበሌው ተመልሶ በተደበቀበት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ተወካይ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ሻለቃ ናቃቸው አቸነፈ በበኩላቸው በወረዳው በርካታ አጋች ግለሰቦችን በመከታተል ለህግ አቅርበን አስቀጥተናል፣ ለወደፊትም አንድም ግለሰብ በእገታ ወንጀል ተደራድሮ ብር እንዲከፍል ፍቃደኛ አይደለንም፤ ለዚህ ትግላችን ማህበረሰቡ ከጎናችን በመቆም መረጃ በመስጠት ሊተባበረን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የመረጃው ምንጭ_የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ነው።
Source: Link to the Post