የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር ማኅበረሰብ ጋቦንን ከአባልነት አገደ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-b01e-08dbaf201b54_tv_w800_h450.jpg

የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ(ECCAS)፣ በኢኳቶሪያል ጊኒ ጂብሎሆ ከተማ ባካሔደው አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባ፣ ጋቦንን ከኅብረቱ አባልነት አግዷታል፡፡ ፖለቲካዊ ግጭቶችን በኀይል የመፍታት አካሔዶችንም መሪዎቹ አውግዘዋል፡፡

ሞኪ ኢድዊን ኪንዴዜጋ፣ ከካሜሩን ዋና ከተማ ያውንዴ ያጠናቀረው ዘገባ፣ ከአንድ ሳምንት በፊት በመፈንቅለ መንግሥት ስለተወገዱት የጋቦኑ ፕሬዚዳንት ዓሊ ቦንጎ ብዙም እንደማይሰማ ያመለክታል፡፡

ቦንጎ ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ርዳታ ከተማፀኑበት በቪዲዮ የተቀረጸ መልዕክት ወዲህ ታይተው አያውቁም፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)

Source: Link to the Post

Leave a Reply