የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት ውስጥ 513 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት አስር ወራት ለውጭ ገብያ ከቀረቡ የተለያዩ ማዕድናት 6 ሺህ 7…

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት ውስጥ 513 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት አስር ወራት ለውጭ ገብያ ከቀረቡ የተለያዩ ማዕድናት 6 ሺህ 785 ነጥብ 42ኪሎ ግራም ማዕድን ለውጭ ገቢያ ቀርቦ 513 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብሏል።

ይህም ለውጭ ገብያ ለማቅረብ ከታቀደው 5 ሺህ 921 ነጥብ 52 ኪ.ግ የማዕድን ምርት እንዲሁም ከሚላከው ምርት ለማግኘት ከታቀደው 501.73 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ብልጫ እንዳለዉ አስታዉቋል።

ይህ ገቢ የተገኘው ከባህላዊ ማዕድን አምራቾች ጀምሮ መካከለኛ እና ከፍተኛ የማዕድን አምራች ኢንዲስትሪዎች ድረስ አበርክቷቸው የጎላ መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስተር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአስገኘው ገቢ ባሻገር የሀብት ብክነት ባሳዩ የማዕድን ልማት ላይ ለመስራት ፍቃድ የወሰዱ ከዚህ ቀደም 63 ተቋማት ፍቃዳቸው የተሰረዘ ሲሆን በድጋሚ በተደረገ ማጣራት 27 የማዕድን አውጪ ተቋማት ከዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ፍቃዳቸው ተሰርዟል፤ እንዲሁም ለ3 የማዕድን አውጪ ተቋማት ስህተታቸውን አርመው ወደ ስራ እንዲገቡ በአፋጣኝ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጨምረው ገልጸዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply