የማዕድን ሚኒስቴር የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ የማፈላለግ ስራ ላይ ከተሰማራው ፖሊ ጂ ሲ ኤ ል ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የገባውን ውል አቋረጠ። የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ በሰጡት መ…

የማዕድን ሚኒስቴር የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ የማፈላለግ ስራ ላይ ከተሰማራው ፖሊ ጂ ሲ ኤ ል ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የገባውን ውል አቋረጠ።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ከኩባንያው ጋር የነበረው ውል ከትናንት ጀምሮ የተቋረጠው ከረጅም ጊዜ ትእግስት እና ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የነዳጅ ሀብቱን ወደ ስራ የሚያስገቡ አፋጣኝ ስራዎችን እንሰራለን ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply