የማይናማር መሪ አውንግ ሳን ሱኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 የአውንግ ሳን ሱኪ የመጀመሪያው የችሎት ውሎ የቀድሞዋ የማይናማር መሪ አውንግ ሳን ሱኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰማ:: ባለፈው ፌብሯሪ ወር መግቢያ ላይ በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው የተወገዱት መሪዋ ለ4 ወራት በእስር ሲቆዩ ችሎት ቀርበው አያውቁም፡፡ ችሎት ፊት ከመቅረባቸው በፊት ለ30 ደቂቃ ያህል ጠበቆቻቸው ጋር እንዲወያዩ የተፈቀደላቸው ሱኪ የጤንነታቸው ሁኔታ መልካም መሆኑን ጠበቆቻቸው ተናግረዋል፡፡

ከፈቃድ ውጭ የመገናኛ ሬዲዮ ይዘው ከመገኘት እስከ ጥብቅ ሚስጥሮችን ማባከን በሚደርሱ ወንጀሎች ክሶች የተመሰረቱባቸው አውንግ ሳን ሱኪ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ 14 ዓመት እስር ይጠብቃቸዋል እየተባለ ነው፡፡ በመፈንቅለ መንግስት ሱኪንና የስልጣን አጋሮቻቸውን ከስልጣን ያስወገደው የማይናማር ወታደራዊ ጁንታ በከፍተኛ ብልጫ ሱኪ ያሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ሰርዞ ሌላ ምርጫ ለማካሄድ አዲስ ኮሚሺን ማቋቋሙ ተነግሯል፡፡

ሀገሪቱን በጊዜያዊነት የሚመራው የሀገሪቱ ጦር ሃይል የቀድሞዋ መሪ ሳን ሱኪ ይመሩት የነበረውን ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ ፓርቲን ሊያፈርሰው እንደሆም ይፋ አድርጓል፡፡ ሮይተርስ እደዘገበው በማይናማር የመፈንቅለ መንግስት መካሄዱን ተከትሎ ከተቀሰቀሰው አመፅ ጋር በተገናኘ እስካሁን ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች መታስራቸው ታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply