#የማጅራት ገትር (Meningitis) የማጅ…

#የማጅራት ገትር (Meningitis)

የማጅራት ገትር በሽታ ዋነኛ የአለም የህዝብ-ጤና ፈተና ሆኖ መቀጠሉ ይነገራል፡፡
የማጅራት ገትር ከፍተኛ የሆነ የሞት መጠን ያለው ወደ ከባድ የረጅም ጊዜ ችግር ሊያመራ እንደሚችል ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡

የማጅራት ገትር ወረርሽኞች በአለም ላይ በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ላይ መታየታቸውንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ስለማጅራት ገትር በሽታም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም በላንሴት ብሄራዊ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ጥገና ማዕከል የነርቭ ህክምና ስፔሻሊስት ከሆኑት ዶ/ር ፍቅሩ ፀሀይነህ ጋር ጣቢችን ቆይታ አድርጓል ፡፡

#ማጅራት ገትር (Meningitis) ምን ማለት ነው?

የማጅራት ገትር የምንለው በተለምዶ ከመገለጫው ጋር ተያይዞ በህመሙ የተጠቁ ሰዎች አንገታቸውን ማጠፍ ስለሚቸገሩ የማጅራት ገትር በሽታ ይባላል ይላሉ ባለሙያው፡፡
ማጅራት ገትር ህመም አንጎል እና ህብረሰረሰርን ሸፍኖ የሚይዝ እንደሽፋን ያለ ቀጭን የሰውነታችን ክፍል ላይ ኢንፌክሽን ሲፈጠር እንደሚመጣ ይናገራሉ፡፡

#መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?

– ባክቴሪያ
– ቫይረስ
– ፈንገስ
– እንዲሁም ሌሎች እሱን የሚያመጡ ህመሞች እንዳሉ እና በይበልጥ የተለመደው የማጅራት ገትር በሽታ በባክቴሪያ ሚመጣ መሆኑን አንስተዋል፡፡

#ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

አብዛኛው የማጅራተት ገትር በሸታ ምልክቱ ተመሳሳይ ሲሆኑ ከነዛም ውስጥ
– አንገትን ለማንቀሳቀስ ገደብ ማስከተል እና ህመም ማምጣት
– ሀይለኛ የሆነ እራስ ምታት
– ብርሀን ለማይት መቸገር
– ከፍተኛ ትኩሳት ይጠቀሱበታል

ማጅራት ገትር በወረርሽኝ መልክ የሚከሰትባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ እና ይህም ወቅትን ጠብቀው የሚመጡ እንደሆኑ ዶ/ር ፊቅሩ ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም በወረርሽኝ መልክ ሲከሰት ተላላፊ ይሆናል ይህ ሲባል ግን ሁሉም የማጅራት ገትር በሽታ ተላላፊ ናቸው ማለት አይደለም ይላሉ ፡፡
አንድ ሰው ይህ ችግር ካጋጠመው የመስማት አቅሙ ሊቀንስ ፣እይታ ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል እና በተለይ በልጅነት እድሜ ላይ የሚከሰቱት መስማት ላይ ዘላቂ የሆነ ችግር ሊያደርስ እንደሚችል አንስተው ባፋጣኝ ወደህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

#የሚደረጉ ህክምናዎች ምንድን ናቸው?

– አካላዊ ምርመራ ማድረግ
– የደም ምርመራ
– ከጀርባ ላይ የማጅራት ገትር ዋና መገለጫ ከሆነው “cerebrospinal fluid” ናሙና ተወስዶ ከዛ ላይ ምርመራ ይሰራል፡፡
– እንደየ ታካሚው የ”MRI” እንዲሁም የ” CT scan” ምርመራ ይደረጋል።
እነዚህ ምርመራዎች ከተደረጉ በኋላ መንስኤው ተለይቶ እንደየ መንስኤው ህክምናውም የተለያየ ስለሆነ የተለያዩ ህክምናዎች እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የማጅራት ገትር በጣም አሳሳቢ ከሚባሉ የነርቭ ስርአት ላይ ከሚከሰቱ ህመሞች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በቤት ውስጥ እንዲሁም በራሳችን ሊደርጉ የሚችሉ ህክምናዎች ባለመኖራቸው ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ ተገቢውን ህክምና የማያገኝ ከሆነ ለህልፈተ ህይወት እስከመዳረግ ሊያደርስ ስለሚችል ህክምናው በሆሰፒታል ደረጃ መደረግ ያለበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

እንዲሁም የማጅራት ገትር በሽታ በወረርሽኝ ደረጃ ሲከሰት ያንን ለመከላከል የሚሰጡ ክትባቶችን መውሰድ እንደሚያስፈል እና ምልክቶቹን በሚያዩበት ግዜ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ምርመራውን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ፍቅሩ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ሚያዝያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply