You are currently viewing የሜቄዶንያው ቢኒያም በለጠ (የክቡር ዶ/ር) የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣    በትምህርቱ የተመሰገነው ወጣት ለቤተሰቦቹ ከ 10 ልጆች 6ኛ ሲሆን ከቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት…

የሜቄዶንያው ቢኒያም በለጠ (የክቡር ዶ/ር) የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በትምህርቱ የተመሰገነው ወጣት ለቤተሰቦቹ ከ 10 ልጆች 6ኛ ሲሆን ከቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት…

የሜቄዶንያው ቢኒያም በለጠ (የክቡር ዶ/ር) የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በትምህርቱ የተመሰገነው ወጣት ለቤተሰቦቹ ከ 10 ልጆች 6ኛ ሲሆን ከቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ሲመረቅ ውጤቱ 4.00 ነበር እናም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ተቀላቅሎ ሕግ አጠናና ለ 3 ዓመታት በሕግ ባለሞያነት በአገር ውስጥ አገልግሎ ወደ አገረ አሜሪካ ተጓዘ፡፡ እዚያም የተለያየ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ ሁለተኛ ዲግሪውን በ Non-profit management and development አገኘ። በ 1970ዓ ከእናቱ ጽጌ በቀለ እና ከአባቱ በለጠ አዲስ በአዲስ አበባ የተወለደው እና “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው…” በሚለው መሪ ቃሉ የምናውቀው ሜቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ድርጅት መስራች እና የሰብአዊ አገልግሎት ሰጪ ግልሰብ ነው፡፡ ይሄ ደግ ሰው የአረጋውያን መውደቂያ ማጣት እንዲሁም በየመንገዱ ወድቆ ጧሪ ቀባሪ ማጣት ያሳስበው ነበርና በአገረ አሜሪካ የተማረውን እውቀት እና ያጠራቀመውን ገንዘብ ይዞ አስታዋሽ ላጡ ሊደርስ የቅንጦት እና የምቾት ሕይወቱን ትቶ ወደ አገር-ቤት ተመለሰ። በ1992/93 ዓ.ም መቄዶንያ የተሰኘ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል በመክፈት 20 ደጋፊ ያጡ ሰዎችን በወላጆቹ ቤት ማኖር ጀመረ፡፡ መቄዶንያ አሁን ትልቅ የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎት መስጫ ሆኖ ከ 4 ሺህ በላይ ሰዎችን ይረዳል። ይህ ሰው ዘመናዊ ህይወቱን ትቶ ለተጎዱ፣ አጋዥ ለሌላቸው እንዲሁም የአካል ጉዳት ላለባቸው አረጋውያን ድጋፍ እየሰጠ ነው። ያደለው ሁሉ ያረጃል፤ እድሜ ጸጋ ነው፡፡ ግን ስናረጅ ያዘጋጀነው ሀብት ከሌለን ወይም የሚጦረን ቤተሰብ ካላፈራን አወዳደቃችን አያምርም ይሄ የአደባባይ ምስጢራችን ነው!! ቢኒያም በአገራችን ካሉ በጎ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው፤ በሱ መኖር የብዙዎች ሕይወት ተቃንቷል… በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በዘመናቸው ማምሻ ላይ ከማልቀስ ድነዋል፤ በክብር በኖሩበት ዓለም ከማፈር ተረፈዋል፡፡ መማሩን፤ ማንበቡን፤ ማስተዋሉን ለመልካም ያዋለ ለሁላችን አርአያ መሆን የሚችል ቅን ሰው… ማንበብ እና መማራችን ለበጎነት እንደዚህ ሲውል ያስደስታል። ስንቶቻችን የተደላደለ ኑሯችንን እንዳናጣ ስንቱን እንበድላለን፤ እሱ ግን ምቾቱን ለብዙ ደሃዎች ሰጠ… እውነትም “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው…” © ማራኪ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply