የምሥራቅ ኢትዮጵያ ፀጥታ ጉዳይ

በኦሮምያና በሶማሌ ክልል አጎራባች አካባቢዎች “በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ ተወስዶበታል” ያሉት “ኦነግ ሸኔ” ብለው የጠሩት ቡድን “ከዚያ ሸሽቶ ድሬዳዋ ገጠር ቀበሌ ለመግባት ሲሞክር ተከታይ እርምጃ ተወስዶበታል” ሲል ፖሊስ አስታውቋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ አያይዞም ከ5 ቀን በኋላ የሚውለው የቁልቢ ገብርዔል በዓለ ንግሥ ያለፀጥታ ሥጋት እንዲከበር ለማስቻል ከኦሮምያ፣ ከሃረሪና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል።

እራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” ብለው ከሚጠሩት አማፂ ታጣቂዎች የተገኘ ምላሽ የለም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply