የምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሊደለደል ያሰባቸው በ192 ምልክቶች አነጋጋሪ ሆነዋል፡፡ (አሻራ ጥር 15፣ 2013 ዓ.ም) ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች 192 ምልክቶችን የመረጠ ሲሆ…

የምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሊደለደል ያሰባቸው በ192 ምልክቶች አነጋጋሪ ሆነዋል፡፡ (አሻራ ጥር 15፣ 2013 ዓ.ም) ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች 192 ምልክቶችን የመረጠ ሲሆን፣ አንዳንድ ምልክቶች ግን በኢትዮጵያን ባህል በሚሰጣቸው ማህበራዊ ትርጓሜ ምክንያት ለፖለቲካ ውክልና አስቸጋሪ ሳይሆኑ አልቀሩም፡፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንዳስነበበው ለምሳሌ ውሻ፣ አህያ፣ ቀበቶ የምርጫ ምልክትነት ተመርጠዋል፡፡ የአህያ ምልክት ያለው ፓርቲ በቅስቀሳ ወቅት ” አህያን ምረጡ” እያለ ሲቀሰቅስ ማህበረሰባዊ ወጉ ችግር ያደርስበታል እየተባለ ነው፡፡ ጡጦ፣ ሙዝ፣በሬም ለምርጫ ምልክትነት የቀረቡ ሲሆን ከምግብ አይነቶች በርገርም የምርጫ ምልክት ሆኖ መጥቷል፡፡ ህግ መንግስቱ ሲረቅ በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ላይ ከኮከቡ ይልቅ አህያ ቢሆንበት መቻቻልን ያሳያል የሚል ሀሳብ ተነስቶ እንደነበር ሰነዶች ያሳያሉ፡፡ የኢህአዴግ መለያ የነበረችው ንብ አሁንም የምርጫ ምልክት ሆኗ የመጣች ሲሆን፣ ድመትም በምርጫ ቦርድ በምልክትነት ተመርጣለች፡፡ ድመትን ምልክት ያደረገ ፖለቲከኛ ሱፉን ለብሶ ” ድመትን ምረጡ ” እያለ ከመጋቢት ጀምሮ ይቀሰቅሳል ማለት ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር መብዛት ምልክትን እንደ ቻይና ስም ሳያስወድደው እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡ ቻይናውያን በስም መመሳሰል እና በስያሜ ማነስ ብዙ ጊዜ ይቸገራሉ፡፡ ኬክ፣ ባልዲ፣ መጥረጊያ፣ አውሮፕላን፣ ዲሽ፣ ፈረስ፣ ጥንጨል፣ ቃሪያ፣ መቀስ፣ መጋዝ፣ ቁልፍ፣ ጫማ፣ እናት፣ ልብ፣ አሳ፣ ዝሆን ወዘተ የምርጫ ምልክት ሆነው የተመረጡ ሲሆን ኢዜማ የልብ ምልክትን መርጧል፡፡ በቀጣዮ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች ብዛት 52 ብቻ ሲሆን፣ ህወኃት፣ ቅንጂት፣ ኢዴፓ እና ኢሃን ከቀጣዮ ምርጫ አይሳተፉም፡፡ ተሰረዘዋል፡፡ ለአብነት በምርጫ ቦርድ መረጃ መሰረት ፓርቲያቸው የተሰረዘባቸው ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እና አቶ ልደቱ አያሌው በቀጣዮ ምርጫ አይሳተፉም፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply