የምርጫ ቦርድ ውሳኔዎች

https://gdb.voanews.com/208732E3-904F-441D-9C5F-C14642AF4C63_cx0_cy3_cw0_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን ምርጫ ካልተደረገባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች መካከል በሶማሌ፣ በደቡብና ሀረሪ ክልሎች መስከረም 20 ቀን ምርጫው እንዲካሄድ መወሰኑን አስታወቀ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የክልልነት ድምጸ-ውሳኔም በዚሁ ዕለት ይከናወናል ተብሏል። ቦርዱ ከዚህ በፊት ከሀረሪ ክልል ጋር እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ በተካሰሰባቸው የሀረሪ ልዩ ምርጫ ጣቢያዎች ዝግጅትን በተመለከተም አስቀድሞ በተካሄዱ ምርጫዎች ይደረግ እንደነበረው ሐረሪዎች ብቻ የሚመዘገቡባቸውና የሚመርጡባቸው የምርጫ ጣቢያዎችን በሀረሪ ክልልና ከሀረሪ ክልል ውጪም እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል። ቦርዱ አስቀድሞ ጳጉሜ ላይ ሊያካሂድ የነበረው ምርጫ በጊዜ ጥበት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመመካከር ወደ መስከረም 20 መሸጋገሩን ቦርዱ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply