የምርጫ ቦርድ የወንበር ብዛት ከወቅቱ ጋር መመጣጠን አለመቻሉ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ (አሻራ ጥር 16፣ 2013 ዓ.ም) የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወንበር በ1987 ዓ.ም እንደፀናው 547 አካባ…

የምርጫ ቦርድ የወንበር ብዛት ከወቅቱ ጋር መመጣጠን አለመቻሉ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ (አሻራ ጥር 16፣ 2013 ዓ.ም) የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወንበር በ1987 ዓ.ም እንደፀናው 547 አካባቢ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ አማራ እና ኦሮሞ 317 ቱን ወንበር ይይዛሉ፡፡ አማራ 138 ተወካይ ሲኖረው፣ ኦሮሚያ ክልል 179 ተወካይ አለው፡፡ ደቡብ 113 ያለው ሲሆን፣ አዲስ አበባ 33 ተወካይ አለው፡፡ ተወካዮች በብዛት ከገጠር ወረዳ የሚወከሉ ሲሆን ለምሳሌ አማራ ክልል 138 ተወካይ አለው ማለት በወቅቱ ክልሉ 138 ወረዳ ነበረው ማለት ነው፡፡ በኢህአዴግ አደረጃጀት መሰረት ወረዳ እንጂ ዞን የፖለቲካ ትርጉም የለውም፡፡ የብሄረሰብ ዞን ካልሆነ በስተቀር የክልልም ሆነ የፌዴራል ምክርቤት የለውም፡፡ ዞንን ህገመንግስቱ አያውቀውም፡፡ በህገመንግስቱ የሚታወቁት ደክልል እና የወረዳ አደረጃጅቶች ናቸው፡፡ በአማራ ክልል የወረዳዎች ቁጥር ወደ 190 የተጠጋ ቢሆንም እስካሁን ከ50 በላይ ወረዳዎች የህዝብ ተወካይ የላቸውም፡፡ በተለይ አዲስ የሚመሰረቱ ወረዳዎች የፌዴራል ውክልና አያገኙም፡፡ በዚህም እነ አፋር፣ ሶማሊያ፣ አዲስ አበባ ወዘተ የምርጫ ወንበራቸው ቁጥጥር እንዲሻሻል ቢጠይቁም ምርጫ ቦርድ ጥያቄያቸውን በአወንታ አልተቀበለውም፡፡ በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች አንድ አንድ ተወካይ ቢኖራቸው የህዝብ ተወካዮች ቁጥር በዕጥፍ ጨምሮ ከ547 ወደ 1 ሺ ከፍ ሊል ይችል ነበር፡፡ የሀገሪቱ አደረጃጀት ካልተቀየረ በቀር ብዙዎቹ ወኪል አልባ መሆናቸው የሚቀጥል ሲሆን፣ ለምሳሌ አዲስ አበባ በህገመንግሥቱ አንድ ክልል ብትሆንም የፌዴሬሽን ምክርቤት ወንበር የላትም፡፡ የፌዴሬሽኑ ምክርቤት ወንበርን የሚሰጠው ብሄር ለሆነ እንጂ ለዜግነት አለመሆኑ በብዛት ከተሞች ወኪል አልባ ናቸው፡፡ ለአብነት አዲስ አበባ እና ድሬድዋ በራሳቸው ክልል ስለሆኑ፣ ክልልነታቸውም በብሄር ሳይሆን በዜግነት ስለሆነ ወኪል አልባ ሆነዋል፡፡ የቡድን እና የዜግነት መብትን ማመጣጠን አለመቻሉ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ዳርጓል፡፡ ወረዳዎች እያደጉ እና ህዝቡ እየጨመረ ስሄድ ልዮ ልዮ የህግ ማሻሻያዎች ይደረጉ ቢባልም፣ መንግስት ተቸክሎ መቅረቱ ተገቢ ውክልናን አሳጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አማራ በዘንድሮው ምርጫም ከአማራ ክልል ውጭ የፖለቲካ ውክልና እንዳያገኝ እየተደረገ ሲሆን፣ ይህም ብልፅግናን በአፈፃፀም የኢህአዴግ ቅጂ አስመስሎታል፡፡ በብልፅግና አፈፃፀም መሰረት ነባር እና መጤ፣ ሀገር አልባ ባለሀገር መሆን ቅርብ ሆኗል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply