You are currently viewing የምስራቅ አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ የነበረው ፋኖ እስራኤል እሸቴ መታሰሩ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ አ…

የምስራቅ አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ የነበረው ፋኖ እስራኤል እሸቴ መታሰሩ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ አ…

የምስራቅ አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ የነበረው ፋኖ እስራኤል እሸቴ መታሰሩ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ የነበረው ፋኖ እስራኤል እሸቴ በተለያዩ ጊዜያት ከእነ ወንድሙ በመንግስት የጸጥታ አካላት ሲደርስበት የነበረውን ማሳደድ እና ወከባ ከአሁን ቀደም በተለይም ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር በነበረው ቆይታ መግለጹ ይታወሳል። አማራ በተለያዩ አካባቢዎች በትሕነግ የሽብር ቡድን ወረራ እየተፈጸመበት በነበረበት አደገኛ ወቅት እንኳ ሳይቀር በመንግስት የጸጥታ አካላት ከመሳደድ አልተረፈም። ፋኖ እስራኤልን በአንድ ወቅት የጦር መሳሪያህን አስመዝግብ በሚል ከቀጠሩ በኋላ መንገድ ላይ ደፈጣ በማድረግ ጥቃት ሊፈጽሙበት መሆኑን ቀድመ መረጃ ስለደረሰው ከግድያ እና ከአፈና መትረፉን ለአሚማ ተናግሮ ያውቃል። ከቀናት በፊት ትፈለጋለህ በሚል ተይዞ በኮምቦልቻ ከተማ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተገልጧል። ይህ የሚያሳዬው የአማራ ፋኖን ማሳደዱ እና ማሰሩ አሁንም ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ ነው። በሸዋ ፋኖዎች ላይ የሚደረገው እስርም ተጠናክሮ ቀጥሎ ከሰሞኑ ሱራፍኤልንና አከላቴ የተባሉ ፋኖዎች “መሳደቡን ረስቶ ተሰድቤያለሁ” ባለው በአቶ ግርማ የሽጥላ ምክንያት መታሰራቸውንና በነጻ የተሰናበቱት 4 የአማራ ፋኖ በይፋት አባላትም ይግባኝ የተጠየቀባቸው መሆኑ ይታወቃል። በተያያዘ የግፍ እስረኛዉ ፋኖ ኢንጅነር እስቲበል አለሙ የዋስትና መብቱን ለማስጠበቅ ህዳር 9/2015 ዓ.ም በባህርዳር ፍ/ቤት ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እንደሚቀርብ ተሰምቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply