You are currently viewing የምስራቅ አማራ ፋኖ አሸባሪው ትሕነግ በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የፈጸመውን የወረራ ጦርነት በመመከት ብሎም ድባቅ በመምታት ሂደት በክብር የተሰው ጀግኖች ስም ዝርዝር ለህዝብ አሳውቋል።  አ…

የምስራቅ አማራ ፋኖ አሸባሪው ትሕነግ በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የፈጸመውን የወረራ ጦርነት በመመከት ብሎም ድባቅ በመምታት ሂደት በክብር የተሰው ጀግኖች ስም ዝርዝር ለህዝብ አሳውቋል። አ…

የምስራቅ አማራ ፋኖ አሸባሪው ትሕነግ በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የፈጸመውን የወረራ ጦርነት በመመከት ብሎም ድባቅ በመምታት ሂደት በክብር የተሰው ጀግኖች ስም ዝርዝር ለህዝብ አሳውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ አማራ ፋኖ አሸባሪው ትሕነግ በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በወሎ ራያ በኩል የፈጸመውን ተከታታይ የወረራ ጦርነት በመመከት ብሎም ድባቅ በመምታት ሂደት ወቅት ድል ያለመስዋዕትነት አይገኝምና በርካታ ጀግኖች በክብር የተሰውበት መሆኑ ይታወቃል። የምስራቅ አማራ ፋኖ ጥቅምት 27/2015 የአማራ ወጣቶች ማህበር ራያ ጢነኛ ሲቪክ ማህበር ባዘጋጀው ደማቁ የዝክረ ሰማዕታት መርኃ ግብር ላይ በተለይም ከ ጀምሮ በነበረው ከፍተኛ ተጋድሎ ወቅት:_ ስለ ራያ፣ ስለ ወሎ ቤተ አምሐራ፣ ብሎም ስለ ሰፊው የአማራ ህዝብ እና ስለ ሀገር ሲሉ በተጋድሎ ወቅት በክብር የተሰውትን ጀግኖችን ስም ዝርዝር ለህዝብ አሳውቋል። ምስራቅ አማራ ፋኖ በአሸባሪው ትሕነግ በኃይል ከአሁን ቀደም የተወሰዱበትን አማራዊ ማንነት እና የአጽመ እርስት ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ በማንሳታቸው የጅምላ ፍጅት፣መፈናቀል እና ስደት ሲፈጸምባቸው የነበሩ አካባቢዎችን ከመከላከያ ሰራዊት፣ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ከፋኖዎች፣ከሚሊሾችና ከመላው የአማራ ህዝብ ጋር በመሆን በሚያውቀው ዱር እና ገደል፣ሜዳ እና ሸንተረር ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ የራያ አማራዎችን የማንነትና ታሪካዊ የአጽመ እርስት ጥያቄዎችን በማስመለስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወቃል። የምስራቅ አማራ ፋኖ ስለ ሀገር እና ስለ ወገን ሲሉ በቁርጠኝነት ደም እና አጥንታቸውን በመገበር ደማቅ ታሪክ በጻፉ አመራሮቹ፣ አባላቱና ማህበረሰቡ የተነሳ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍ ያለ ታሪካዊ አሻራ ማስቀመጡ ግልጽ ነው። ስለአማራነት የተከፈለውን መስዋዕትነት ለማሳዬትም የባለፈው ዓመት መስዋዕትነት እንዳለ ሆኖ በተለይም ከሰኔ 15/2014 ዓ/ም ጀምሮ በሁለተኛው ዘመቻ ህልውና ወቅት የሽብር ቡድኑን ወረራ ለመቀልበስ የተከፈለውን የክብር መስዋዕትነት የተሰው ጓዶችን ስም ዝርዝር በማስፈር ለህዝብ አሳውቋል። እያንዳንዱ ድርድርም ሆነ ንግግር የህዝቡን የዘመናት ጥያቄ እና የተከፈለውን ታላቅ የክብር መስዋዕትነትን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን እንደሚገባውም የተለያዩ አስተያዬቶች እየተሰጡ ነው። ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት ይሁን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply