You are currently viewing የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የአማራ ልዩ ኃይል በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ የገነቴ ከተማን ነጻ አወጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸ…

የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የአማራ ልዩ ኃይል በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ የገነቴ ከተማን ነጻ አወጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የአማራ ልዩ ኃይል በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ የገነቴ ከተማን ነጻ አወጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከምስራቅ አማራ ፋኖ ለአሚማ የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ህዳር 23 ቀን 2014 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ተኩል ላይ ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በተቀናጀ መልኩ ባደረጉት ተጋድሎ በደደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ የገነቴ ከተማ ነጻ ለማውጣት ተችሏል። ላለፉት 10 ቀናት በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ስር የነበረችው እና በቁርጥ ቀን የአማራ ታጋዮች ዛሬ ነጻ የወጣችው ገነቴ ከተማ ሼህ ጀማል የተባለ አባት በወራሪዎች የተገደለባት መሆኑ ይታወቃል። ሼህ ጀማል ከሱቃቸው እያሉ ነበር በአሻሪው ቡድን አባላት ገንዘብ በመጠየቅና ሽጉጣቸውን በመቀበል በገዛ ሽጉጣቸው ነበር በአፋቸው ተኩሰው የገደሏቸው። ገነቴ ከተማ የመንግስትና የግለሰብ ተቋማት፣ ባንክና የማደበሪያ ማከማቻ ተቋም በሙሉ ተዘርፏል። አሚማ እነ ፋኖ ምህረት ወዳጆ (ምሬ) ከሚመሩት ከምስራቅ አማራ ፋኖ ተወካይ እና ነጻ ከወጡት ከገነቴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል። በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይከታተሉ

Source: Link to the Post

Leave a Reply