የምስራቅ ጎጃም ዞን ለመተከል ተፈናቃዮች ባደረገው ድጋፍ የጓንጓ ወረዳ ምስጋና አቀረበ (አሻራ ጥር 01/2013 ዓ.ም ባህር ዳር) የጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ለምስራቅ ጎጃም ዞን የምስጋና…

የምስራቅ ጎጃም ዞን ለመተከል ተፈናቃዮች ባደረገው ድጋፍ የጓንጓ ወረዳ ምስጋና አቀረበ (አሻራ ጥር 01/2013 ዓ.ም ባህር ዳር) የጓንጓ ወረዳ አስተዳደር ለምስራቅ ጎጃም ዞን የምስጋና መልዕክት ያስተላለፈው ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ ከተማ ራንች በሚባለው ቦታ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ከ1.4 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት ለለት ምግብ የሚሆን እህልና ስኳር ድጋፍ በማድረጉ ነው ብሏል ጓንጓ ወረዳ ። ድጋፉንም የጓንጓ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ አለሙ በተገኙበት አስረክበዋል። ድጋፉን ያመጡት የምስራቅ ጎጃም ዞን ማህበራት መም/ ኀላፊ አቶ ሙልቀን ቢያድግልኝ እንደገለፁት ድጋፉ የተሰባሰበው በዞኑ ከሚገኝ የወረዳው ማህበረሰብ እህል በማሰባሰብ የመጣ መሆኑን ጠቅሰው፣ ቀጣይም ወደ ቦታቸው ተመልሰው እስከሚቋቋሙ ድጋፉ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ድጋፉን ለማስረከብ አብረው የመጡት በምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ዘመን ጌቶ በበኩላቸው በቦታው ተገኝተው የተፈናቃዮችን ሁኔታ ተመልክተው ልባቸው በሀዘን መነካቱን ገልፀው ሌሎችም ኢትዮጵያውያን የቻሉትን እንዲያግዙ አሳስበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply