የምስራቅ ጎጃም ዞን የ1.4 ሚሊየን ብር ግምት የተሰጠው  472 ኩንታል እህል ለመተከል ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 30፣ 2013 ዓ.ም) የምስራቅ ጎጃም ዞን ከዚህ ቀደም ለ…

የምስራቅ ጎጃም ዞን የ1.4 ሚሊየን ብር ግምት የተሰጠው 472 ኩንታል እህል ለመተከል ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 30፣ 2013 ዓ.ም) የምስራቅ ጎጃም ዞን ከዚህ ቀደም ለ…

የምስራቅ ጎጃም ዞን የ1.4 ሚሊየን ብር ግምት የተሰጠው 472 ኩንታል እህል ለመተከል ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ፡፡ (አሻራ ታህሳስ 30፣ 2013 ዓ.ም) የምስራቅ ጎጃም ዞን ከዚህ ቀደም ለአማራ ልዮ ሀይል እና ለመካላከያ ከ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ለመተከል ተፈናቃዮች 1.4 ሚሊየን ብር ግምት ያለው 472 ኩንታል እህል ወደ ቻግኒ ተፈናቃዮች እንደላከ የምስራቅ ጎጃም ኮሚኒኬሽን ባለሙያው የጋሻየ ጌታሁን መረጃ ያሳያል፡፡ ዞኑ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አለኸኝ ተናግረዋል፡፡ ድጋፉ በመተከል ባሉ ወረዳዎች ላሉ ተፈናቃዮችም እንዲደርስ በመተከል ያሉ ተፈናቃዮች እያሳሰቡ ሲሆን፣ በመተከል ሞት እና መፈናቀሉ ዛሬም እንዳልቆመ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እንቅስቃሴው በታጣቂዎች በመገደቡ እና የመንግስት መስሪያቤቶችም በደንብ ስራ ስላልጀመሩ ማህበረሰቡ ስጋት ውስጥ ነው፡፡ መተከል የዞን አስተዳዳሪ እስከካሁን አልተሾመለትም፡፡ ኮማንድ ፓስቱ ለአካባቢውን መልካዓምድራዊ እና ባህላዊ ሁኔታ እንግዳ መሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስኬታማ ህግ የማስከበር ስራ አልሰራም፡፡ የመንግስት መዋቅሩም ከታጣቂዎች ጎን በመሆኑ በመተከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ በመተከል በሁለት ወራት ውስጥ ብቻ 170 ሺ ሰው የተፈናቀለ ሲሆን፣ እስካሁን የተመለሰ ሰው የለም፡፡ በቀጣይ የአመራር ስብጥሩ ካልተስተካከለ ጭፍጨፋው ሊቀጥል ይችላልም እየተባለ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply