You are currently viewing “የምትችሉ ተባብራችሁ ብታሳክሙኝ!” ፋኖ ሞላ መንግስቴ አበበ ከዳባት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…    ነሃሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ ፋኖ ሞላ መንግስቴ አበበ…

“የምትችሉ ተባብራችሁ ብታሳክሙኝ!” ፋኖ ሞላ መንግስቴ አበበ ከዳባት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ፋኖ ሞላ መንግስቴ አበበ…

“የምትችሉ ተባብራችሁ ብታሳክሙኝ!” ፋኖ ሞላ መንግስቴ አበበ ከዳባት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ነሃሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ፋኖ ሞላ መንግስቴ አበበ ይባላል። በሰሜን ጎንደር ዞን በእነ ሻለቃ አራጋው ፋኖ ተሰልፎ አሸባሪውን እና ወራሪውን ትሕነግ በቁርጠኝነት የታገለ ነው። ታህሳስ 18/2014 በአዳርቃይ ግንባር ከአሸባሪውና ወራሪው ትሕነግ ጋር በነበረው የተኩስ ልውውጥ መቁሰሉን ገልጧል። በብሬን እጁን የተመታ ሲሆን የእጅ ስብራቱ እየያዘለት ቢሆንም እጁ እንደማይታዘዝለት ገልጧል። ይህም የነርብ ችግር መሆኑ በዶክተሮች ተነግሮኛል ብሏል። በጎንደር ሆስፒታል ለ4 ወራት ከታከመ በኋላ የነርብ ችግር ነው፤ እዚህ ማየት አንችልም ወደ አዲስ አበባ ሂድ ስለመባሉ ይናገራል። በግልህ ወይም በዘመድ ወደ አዲስ አበባ ሄደህ በአለርት ሆስፒታል መታከም ትችላለህ፤ እዚህ አንችልም ስለመባሉ ገልጧል። ህክምናው መጋቢት 25/2014 ጀምሮ ህክምናው መቋረጡን አስታውቋል። እስካሁን የሚረዳው በጎ ፈቃደኛ ሰው አላገኘም። ክፉኛ መቸገሩን ይናገራል። ወራሪን ሲታገሉ የቆሰሉ ጀግና ፋኖዎች የት ወደቃችሁ ብለን እንድንጠይቅም አሳስቧል። ስለአማራ እና ስለ ሀገሬ ስል አሸባሪን ስታገል እጄ ላይ ባጋጠመኝ ምት ቆስያለሁ፤ ይህም የነርብ ችግር ነው ስለተባልኩ ወገን ለወገን ደራሽ ነውና የምትችሉ ወንድም እና እህቶች እባካችሁ ተባብራችሁ አሳክሙኝ፤ ባለትዳር እና እጄን የሚያይ ህጻን ልጅም አለኝ ሲል ፋኖ ሞላ መንግስቴ ወገናዊ ጥሪ አስተላልፏል። መደገፍ የምትፈልጉና የምትችሉ:_ ሞላ መንግስቴ አበበ እባላለሁ። የምኖረው ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ነው። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈተ አካውንት አለኝ። ይኸውም:_1000054207167 አድራሻ_ስልክ_ +251935378154

Source: Link to the Post

Leave a Reply