የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ ሻለቃ ፋኖ አንተነህ ድረስ ታስሮ ውሏል ምክንያቱ “ወልቃይት መሄድ አትችሉም” የሚል ነው። ግንቦት 07/2014/ዓ.ም አሻራ…

የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ ሻለቃ ፋኖ አንተነህ ድረስ ታስሮ ውሏል ምክንያቱ “ወልቃይት መሄድ አትችሉም” የሚል ነው። ግንቦት 07/2014/ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆነው ሻለቃ ፋኖ አንተነህ ድረስ ታስሯል። ምክትል አዛዡን ጨምሮ የምኒልክ ብርጌድ ከፊል አባላትን በመያዝ ወደ ወልቃየት ጠገዴ ለመጓዝ ከጎንደር ዛሬ ማለዳ ተነስተው የነበረ ሲሆን፣ ይሁን እንጅ ምሴባምባ ፧ልዮ ስሙ ፈረስ መግሪያ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ፣ “ወደ ወልቃይት መሄድ አትችሉም”በሚል ከባድ መሳሪያ በመጥመድ ጭምር አግተዋቸው ውለዋል። የብርጌዱ ምክትል አዛዥ ፋኖ መብራቱ ስላለው ሁኔታ ሲናገር ” እኔ የተወለድኩት ወልቃይት ነው፤እውነተኛ ፋኖም ነኝ።ከመንግስት ተለጥፌ ጥቅማጥቅም የማሳድድም አይደለሁም።ብልፅግና ሁን! ዋሽ! ቅጠፍ! ይሉኝ ነበረ።እኔ ግን ለ7 ዓመት የታገልኩት ለአገሬ፣ለሀቅ እና ለሰንደቅ ዓላማየ ነው።መቼም እሞታለሁ እንጅ ለጥቅም ብየ ከውሸት ጋር አልቆምም “በማለት መልሸላቸዋለሁ ብሏል። አያይዞም “ብልፅግናዎች ስብሰባ ሲጠሩ እኛን አይጠሩንም፤ ለዕውነት የቆምን መሆኑን ስለሚረዱ። ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ትጥቅ ለማስፈታት ሞክረው ነበረ።አልቻሉም እንጅ።ለማንኛውም ነገ እኔ ብሞት ህዝብ ማወቅ ያለበት ለዕውነት ብቻ መሆኑን ነው” ብሏል። በየጊዜው በፋኖ ላይ የሚደርሰው እንግልት እና ውክቢያ እየተጠናከረ ቢመጣም፣ ሰለ አካባበው ሰላም ስንል መታገስን መርጠናል ብለዋል። ©ባልደራስ

Source: Link to the Post

Leave a Reply