You are currently viewing የምኒልክ ብርጌድ የፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ በ10 ሽህ ብር ዋስትና ተፈታ! ተደጋጋሚ የመፍቻ ትዕዛዞች የታጠፉበት የምኒልክ ብርጌድ የፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ በ10…

የምኒልክ ብርጌድ የፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ በ10 ሽህ ብር ዋስትና ተፈታ! ተደጋጋሚ የመፍቻ ትዕዛዞች የታጠፉበት የምኒልክ ብርጌድ የፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ በ10…

የምኒልክ ብርጌድ የፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ በ10 ሽህ ብር ዋስትና ተፈታ! ተደጋጋሚ የመፍቻ ትዕዛዞች የታጠፉበት የምኒልክ ብርጌድ የፋኖ ዋና አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ በ10 ሽህ ብር ዋስትና ተፈቷል። “ታጥቃችሁ ወደ ወልቃይት መሄድ አትችሉም” በሚል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ በእነ አቶ ዳኘ ክልከላ የተደረገባቸው የምኒልክ ብርጌድ ፋኖ አዛዥ ሻለቃ አንተነህ ድረስ ከግንቦት 7/2014 ጀምሮ የግፍ እስር ሲፈጸምበት መቆየቱ ይታወሳል። 1) ሰኔ 3/2014 በ20 ሽህ ብር_ ጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ፣ 2) ሰኔ 22/2014 ታች አርማጭሆ ወረዳ ፍ/ቤት እንዲሁም፣ 3) ሃምሌ 11/2014 አሁንም በሌላ ወንጀል ትፈለጋለህ በሚል በቀረበበት የእምነት ማጉደል ክስ በ10 ሽህ ብር ዋስትና እንዲፈታ የተፈቀደለት መሆኑ ቢታወቅም በተደጋጋሚ ሌላ ክስ አለብህ በማለት ህግን እና ስልጣንን ለማጥቂያነት በሚጠቀሙ ግለሰቦች መብቱ ሲነፈግ መቆየቱ ይታወቃል። ሻለቃ አንተነህ ድረስ መንግስትን መገልበጥ አለብን ስትል ቀስቅሰሃል በሚል ሌላ ክስ በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጎንደር ቋሚ ምድብ ችሎት ሃምሌ 22/2014 ከረፋዱ 5 ሰዓት ቀርቧል። ከአሁን ቀደም በፍርድ ቤት የተፈቀዱ 3 የፍ/ቤት የመፍቻ ትዕዛዞች የተጣሱበት ሻለቃ አንተነህ ድረስ በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት የጎንደር ቋሚ ምድብ ችሎት የሰጠው 4ኛው የዋስትና መብቱ ተከብሮለታል። ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዋስትና ቢፈቀድለት ተቃውሞ የለኝም ማለቱን ተከትሎ ችሎቱ ይፈታ የሚል ውሳኔ አሳልፎ ከእስር ተፈቷል። ሻለቃ አንተነህ ድረስ በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ የፈጸሙ የአሸባሪው ትሕነግ አባላትን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች በመመከትና ድባቅ በመምታት ረገድ በንቃት የተሳተፈ፣ በጫካ እንዲሳደድ ያደረጉት ከምክትል ሻለቃው አርበኛ መብራቱ አረጋ እና ከሌሎች ጓዶቹ ጋር የቡድን መሳሪያዎችን የማረከ መሆኑ ይታወቃል። ©አሚማ ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply