የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች በመስሪያ ቤት ውስጥ የህጻናት ማቆያ አገልግሎት መስጫ ተግባራዊ እንዲሆን የጸደቀ መሆኑን ገለጸ። አማራ…

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች በመስሪያ ቤት ውስጥ የህጻናት ማቆያ አገልግሎት መስጫ ተግባራዊ እንዲሆን የጸደቀ መሆኑን ገለጸ። አማራ…

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች በመስሪያ ቤት ውስጥ የህጻናት ማቆያ አገልግሎት መስጫ ተግባራዊ እንዲሆን የጸደቀ መሆኑን ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለ አሸናፊ እንዳሉት በተሻሻለው የአማራ ብሔራዊ መንግስት አዋጅ ቁጥር 253 /2010 በሚተዳደሩ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሴት የመንግስት ሰራተኞች ከህፃን ልጆቻቸው ርቀው በሚሰሩበት ተቋም ውስጥ ሙሉ ትኩረታቸውንና አቅማቸውን በተሰማሩበት የስራ መስክ ላይ አለማድረጋቸውን ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ከህፃን ልጆቻቸው ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ከስራ ገበታቸው መቅረት በራሳቸው እድገት ፣አቅም፣ ቅልጥፍናና ብቃት፣ በራስ መተማመን ፣ የራሳቸውን የኢኮኖሚ አቅም ከማሳደግ አኳያ ራስን የመቻል እንቅስቃሴያቸው ላይ እያሳደረ ያለው አሉታዊ ተጽእኖ ለመቀነስ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡ ህፃናት እናቶቻቸውን በስራ ምክንያት በአቅራቢያቸው ባለመኖራቸው ማግኘት የሚገባቸውን እንክብካቤ አለማግኘታቸውን በአመጋገባቸው ፣ በጤንነታቸው ፣በደህንነታቸው ፣ በአስተሳሰብ ፣ በቅልጥፍና ፣ በፈጠራ ክህሎት፣ በአካላዊ እድገታቸው ፣በአእምሮ ብስለታቸው እንዲሁም ሀሳብን በነፃነት የመግለጽና የማዳመጥ ሌሎችንም ጨምሮ በህፃናት ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለማሻሻልና የእናቶችንም ጫና ለመቀነስ እንደሚረዳ ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህና መሰል ጉዳቶችን ለመቀነስ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ ወደ ተግባር መግባት ይኖርበታል ሲሉ ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply