የምክንያታዊ ወጣት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

የምክንያታዊ ወጣት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምክንያታዊ ወጣት መድረክ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

መድረኩ የተዘጋጀበት ዋና አላማ “ሙሉ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለሀገራችን ወጣቶችና ለክልላችን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል መሆኑን የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ ተናግረዋል።

ያለፉት ስርዓቶች ብሄር ብሄረሰቦችን አሳታፊ ያላደረጉና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ሙሉ ለሙሉ ያላጎናፀፈ ነበርም ብለዋል ሀላፊው።

አሁን ላይ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ሀገራዊ ጉዳዮች እና ውሳኔዎች ውስጥ የመሳተፍ መብትን አግኝተዋል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽ ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩ በሀገረ-መንግስት እና በብሄረ-መንግስት ፅንሰ ሀሳብና ዓለም አቀፋዊ ልምዶች ዙሪያ የመነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

መድረኩ ከለውጡ ማግስት አንስቶ መንግስት እየሰራቸው የመጡ ስራዎችን በማስገንዘብ በቀጣይ ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች ለማሳወቅ ይረዳል ተብሏል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራኖችን ጨምሮ ለሎች ባለ ድርሻ አካላቶች በመድረኩ ተሳትፏል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳ

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post የምክንያታዊ ወጣት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply