የምዕራቡ ዓለም በተለይ አሜሪካ ለዩጎዝላቭያ መፍረስ ምን አድርጋ እንደነበር የሚያሳይ ጥናታዊ ፊልም ከህወሓት ደጋፊ እስከ የፅንፍ የኦሮሞ ብሔርተኝነት አራማጆች፣ከአማራ አክራሪ ብሔርተኝነት እስከ ኢትዮጵያዊነት ይቅደም የምንል ሁሉ በትዕግስት እንመልከተው።

ፊልሙን ከተመለከትኩ በኃላ እነኝህ ነጥቦችን ያስታውሱ -ኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ግጭቶቿ ታሪካዊ ዳራ እና ስነልቦናው ከዩጎዝላቭያ ጋር አይመሳሰልም።ይህ ማለት ግን ለኢትዮጵያ ካልሰራን አደጋ የለብንም ማለት አይደለም::ዩጎዝላቭያ የነበረው ሕዝብ የመከፋፈል አካሄድ፣ የአሜሪካ እና የምዕራቡ የጣልቃ ገብነት መጠን እና ደረጃዎች በትክክል አሁን እያደረጉት ካለው ጋር ይመሳሰላል።በኢትዮጵያ በብ/ጄ አሳምነው ዙርያ የተነሳው የባህርዳሩ አስዛኝ የአመራሮች ሞት፣የአርቲስት ሃጫሉ መገደል፣በሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት የተወሰደው ማጥቃት ሦስቱ ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ አጋጭቶ ለማፍረስ የመጡ መቅሰፍቶች ነበሩ።እነርሱን አልፈናል።ለቀጣይ

Source: Link to the Post

Leave a Reply