የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ማሊ ላይ ማዕቀብ ጣሉ

የምዕራብ አፍሪካ አገራት መሪዎች በማሊ ላይ አዲስ የንግድና የፋይንናስ እርዳታ ማዕቀብ መጣላቸውን አስታወቁ፡፡ 

አገራቱ ማዕቀቡን የጣሉት መፈንቀለ መንግሥት በተደረገባት ማሊ ያሉት ወታደራዊ መሪዎች በሚቀጥለው ወር ይካሄዳል የተባለውን ምርጫ ለአምስት ዓመት በማስተላለፋቸው ነው፡፡ 

ወታደራዊ የማሊ መንግሥት ምርጫ የሚያካሄዱት ሥልጣን ከቆዩ አራት ዓምታት በኋላ መሆኑን ማስታወቃቸው ተመልክቷል፡፡ 

የምዕራብ አፍሪካ የጋራ ትብብር አባል አገራት መሪዎች ውሳኔውን ያሳለፉት በጋና ዋና ከተማ ቀኑን ሙሉ የፈጀ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ባወጡት መግለጫ መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

የማሊ ውሳኔ ጠቅላላውን የምዕራብ አፍሪካ የሚያሰጋ መሆኑንም አገራቱ በመግለጫቸው ገልጸዋል፡፡ 

ማሊ ከምዕራብ አፍሪካ የትብብር አባል አገሮች ጋር የምታደርገው የየብስ ድንበርና የአየር ግንኙነት የሚቋረጥ መሆኑም በማዕቀቡ መግለጫ ተመልክቷል፡፡ 

Source: Link to the Post

Leave a Reply