የሞያሌን አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ህገወጦችን ከመቀነሱም ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ የኢጋድ የጤና እና የማህበራዊ ልማት ዳይሬክተሯ ፋቲያ አልዋ…

የሞያሌን አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ህገወጦችን ከመቀነሱም ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ የኢጋድ የጤና እና የማህበራዊ ልማት ዳይሬክተሯ ፋቲያ አልዋን ተናገሩ፡፡

ዳይሬክተሯ ይህን ያሉት ኢጋድ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ ድንበር የጀመሩትን የንግድ ትስስር በሚያጠናክሩበትና በልማት ስራዎች ዙሪያ ከአባል አገራቱ ጋር እየመከረ በሚገኝበት ጉባኤ ላይ ነው።

የኢጋድ የጤና እና የማህበራዊ ልማት ዳይሬክተሯ ፋቲያ አልዋን፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ ድንበር የጀመሩት ልማት በአካባቢው የሚገኙ ዜጎችን ህይወትን የሚሻሻል ነው ብለዋል ።
በተለይም በአካባቢውበህገወጥ የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ከመቀነሱም ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋል ነው ያሉት።

የዚህ ስብሰባ ዋነኛ አለማ በኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር በተለይም በሞያሌ አካባቢ የሚገኙ ስደተኞችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሆነ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪም በሁለቱም አገራት ድንበር አካባቢ የሚገኙ ከ1 ሺህ 6 መቶ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ዳይሬክተሯ ፋቲያ አልዋን አስታውቀዋል።

በቀጣይ፣ የምስራቅ አፍሪካ አገራትን በማስተሳሰር ረገድ ኢጋድ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለፁት ፋቲያ፣በተለይም የመተማ ጋለባት አካባቢዎችን ተጠቃሚ ለማድረግና ኢትዮጵያና ሱዳንን ተጠቃሚ ለማድረግ በጋራ እንሰራለን ነው ያሉት።
በመድረኩ፣ ከኢትዮጵያና ኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢጋድ፣ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልል የተወጣጡ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያና ኬንያ የሞያሌን አንድ አለቅ የድንበር አገልግሎት ስምምነት ባለፈው ሳምንት መፈረማቸው የሚታወስ ነው።

በአባቱ መረቀ

መስከረም 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply