የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ኦርቢት ሄልዝ በወጣቶች እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ኦርቢት ሄልዝ በወጣቶች እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ኦርቢት ሄልዝ በወጣቶች እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ።
ሁለቱ ተቋማት ወጣቶችን እና ሥራ ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ፣ የጋራ ተጠቃሚነት እንዲሁም በዘርፉ ጉልህ ሚና ያለው ትብብር እና ግንኙንት ለመፍጠርና አብረው ለመሥራት መስማማታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስምምነቱ ሥራ ፈጣሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ ከማብቃት ባሻገርም በገበያ ላይ ያሉ ሥራ ፈጣሪዎችን አቅም በማሳደግ አውንታዊ ለውጥ እንዲያመጡ እንዲሁም ሀብትን በተናበበ መልኩ መጠቀምና የዲጂታል ፈጠራዎችን ፣ አቅም ግንባታን እና የተለያዩ ተያያዥ ክንውኖችን ያካትታል ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ኦርቢት ሄልዝ በወጣቶች እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply