
ደራሲ ትዕግሥት ወደ ድርሰቱ ዓለም ከመግባቷ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበበችው የአያቷን የግጥም እና የቴአትር ሥራዎችን ነው። አያቷ ደግሞ ከ20 በላይ የሙሉ ጊዜ እና ከ15 በላይ አጫጭር ተውኔቶችን የጻፉ ሁለገብ ከያኒ ናቸው። ትዕግሥት ከአያቷ በመቀጠል ከባሕር ማዶም ከአገር ውስጥ የልብ ወለድ ደራሲዎች ጋር ተዋወቀች። ሁለት መጻሕፍትን ለሕትመት ያበቃችው ደራሲ ትዕግሥት ሳሙኤል ነዋሪነቷ በኔዘርላንድስ ነው። ቢቢሲ በቅርቡ የታተመውን እና አጫጭር ልብ ወለድ ታሪኮች እና ግጥሞቿን የያዘው መጽሐፍን መሠረት አድርጎ ቃለ መጠይቅ አድርጎላታል።
Source: Link to the Post