የሩሲያን ጦር ለመቀላቀል 3 መቶ ሺህ ዜጎች መመዝገባቸውን ፑቲን አስታወቁ፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱን ጦር ለመቀላቀል ዜጎች ኮንትራት እየፈፀሙ ነዉ ብለዋል፡፡

ፑቲን የቤላሩሱ አቻቸዉን አሌግዛንደር ሉካሼንኮን በሶቺ ከተማ ተቀብለዉ ባነጋገሩበት ወቅት፣በዩክሬን ጦርነት ሶስተኛ ወገን አንጋብዝም ሲሉ ነግረዋቸዋል፡፡

ዩክሬን ሶስተኛ ወገኖችን ብትጋብዝም ሩሲያ ግን ይህንን አታደርግም ሲሉ መናገራቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

የዩክሬኑን ጦርነት ለመቋጨት የማንንም ድጋፍ እንደማይፈልጉም ፑቲን ለቤላሩሱ መሪ አረጋግጠዋል፡፡
ለዚህም 3 መቶ ሺህ ዜጎች የጦር ኃይሉን እየተቀላቀሉ ነዉ ብለዋል፡፡

በአባቱ መረቀ

መስከረም 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply