የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ዜጎቻቸዉ ብዙ ልጆች እንዲወልዱ አሳሰቡ፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱ ዜጎች ብዙ ልጆችን እንዲወልዱ በድጋሜ አሳስበዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የሩሲያን ህልዉና ለማስጠበቅ የህዝብ ቁጥራችንን ማሳደግ ይገባል ሲሉ ለህዝባቸዉ ተናግረዋል፡፡

እያንዳንዱ ሩሲያዊ ቢያንስ ሁለት ልጅ መኖር እንዳለበትም ፕሬዝዳነቱ ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡

የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት በ1990ዎቹ የገጠማት አይነት የስነ ህዝብ ዉድቀት እንዳይደገም ማሳሰባቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

ከሁለት ልጅ በላይ ለሚወልዱ የሀገሪቱ ዜጎችም እንደሚበረታቱ ታዉቋል፡፡

በቆዳ ስፋቷ ከአለማችን ቀዳሚ የሆነችዉ ሩሲያ 1 መቶ 45 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አላት፡፡

በአባቱ መረቀ

የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply