የሩሲያ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ቡርኪናፋሶን ጎበኙ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-0293-08dbaaeb413e_w800_h450.jpg

በሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ዩኑስ ቤክ የቭኩሮቭ የተመራ ልኡካን ቡድን ከቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ጋር ትናንት ሀሙስ ተገናኝቶ መነጋገሩ ተገለጸ።

ውይይቱ ወታደራዊ ትብብሮች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተነግሯል።

ጉብኘቱ የቫግነር አዛዥ ይቭጊኒ ፕሪጎዥን ሞት ተከትሎ ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን ተጽእኖ ለማሳደግ ፍላጎት ያላት ስለመሆኑ ማሳያ ነው ተብሏል።

በወታደራዊ ቡድን የምትመራዋ ቡርኪናፋሶ የፈረንሳይ ወታደሮችን ባለፈው የካቲት ካባረረች ወዲህ ከሞስኮ ጋር ያላትን ግንኙነት ትኩረት ሰጥታው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።

የሩሲያ ቅጥረኛው ወታደራዊ ቡድን ቫግነር የቡርኪናፋሶ ጎረቤት በሆነችው እንደ ማሊ ባሉ አገሮችም ውስጥ እንደሚሠራ ተመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply