የሩሲያ ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ በእስር ቤት ውስጥ መሞታቸው ተገለፀ፡፡

የሩሲያ ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ ለዓመታት በቆዩበት የአርክቲክ እስር ቤት ዛሬ አርብ ህይወታቸው ማለፉን የሩሲያ የፌደራል ማረሚያ ቤት አስታውቋል።

የሩሲያ ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ “ከእግር ጉዞ በኋላ መጥፎ ስሜት ተሰምቶት ነበር” ሲሉ የእስር ቤቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ስለሞቱ ምክንያት ግን ምንም ማረጋገጫ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

የአውሮፓ ህብረት፣ ኔቶ እና አብዛኛዎቹ የምዕራባውያን ሀገራት ሩሲያን ለናቫልኒ ሞት ተጠያቂ አድርገዋል።

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ በበኩላቸው የሩሲያ ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ በእስር ቤት በመሞታቸውን “በጣም ማዘናቸውን” ገልፀው፤ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሩሲያ እንደ ሀገር እንዴት እንደተቀየረች የሚያሳይ “አሰቃቂ” ምልክት ነው ብለዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪም ለተቃዋሚው መሪ አሌክሲ ናቫልኒ ግድያ የሩስያውን መሪ ቭላድሚር ፑቲንን ከሰዋል።

ናቫልኒ ከደረሰባቸው የነርቭ መመረዝ ችግር ጀርመን ውስጥ ካገገሙ በኋላ ወደ ሩሲያ ሲመለሱ በጎርጎሪያኑ ጥር 2021 ዓ/ም ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ የ19 ዓመታት እስር ተፈርዶባቸው በማረፊያ ቤት ቆይተዋል።

የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply