የሩሲያ ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ የሚመክረው የሩሲያ ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚ…

የሩሲያ ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ የሚመክረው የሩሲያ ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር የሽሩን አለማየሁ ፎረሙ ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎችም ዘርፎች ይበልጥ እንዲሰሩ የግዛል ብለዋል።

የሩሲያና ኢትዮጵያ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው የሩሲያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕል ነዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ አቅርበዋል።

የሩሲያ ፌዴሬሽን የማዕድን ሀብት የፌዴራል ኤጀንሲ ኃላፊ ኢቭገኒቭ በበኩላቸው በተለያዩ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ሞስኮ ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

በተለይም እያደገ የመጣውን የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ መደገፍ እንደሚገባ አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭገኒ ቴረኪን በበኩላቸው የሩሲያ መንግስት በብዙ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ዝግጁ ነው ብለዋል።

በመድረኩ ላይ ከንግዱ ማህረሰብ ፣ከማዕድንና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተወከሉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በአባቱ መረቀ
ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8)

Source: Link to the Post

Leave a Reply