
በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ፌዴሬሽን ኤምባሲ ትናንት ሚያዚያ 11/2014 ባወጣው መግለጫ ምንም አይነት የውትድርና ምልመላ ጥያቄዎችን አልቀበልም አለ። ኤምባሲው ይህን ያለው “አስፈላጊ በሆነው መንገድ ሁሉ” ከሩሲያ ጎን እንቆማለን ያሉ ኢትዮጵያውያን ከኤምባሲው ፊት ለፊት በብዛት ተሰልፈው መታየታቸውን ተከትሎ ነው። የቢቢሲ ዘጋቢዎች በኤምባሲው አካባቢ በርካታ ወጣቶች የተለያዩ ሰነዶችን ይዘው ተሰልፈውና ቆመው ተመልክተዋል።
Source: Link to the Post