የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ኤርትራን ጎበኙ

https://gdb.voanews.com/09320000-0a00-0242-bda9-08daffb88a5d_w800_h450.jpg

በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የተመሩ ከፍተኛ ልዑካን በኤርትራ የአንድ ቀን ጉብኝት ለማድረግ ምጽዋ የገቡት ዛሬ ጠዋት ሲሆን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሚኻዬል ቦግዳኖቭም አብረዋቸው ተጉዘዋል፡፡

ልዑካኑን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳልህ ፕሬዚዳንታዊ አማካሪው የማነ ገብረ መስቀል በኤርትራ የሩስያ አምባሳደር ኢጎር ሞዝጎ እና ሌሎችም ከፍተኛ የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናት በምጽዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ላቭሮቭ በቆይታቸው ከኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተው የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነቶች ስለማጠናከር እንዲሁም የሁለቱ ሀገሮች ትኩረት በሆኑ የቀጣናው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተው የአንድ ቀን ጉብኝታቸውን ማጠናቀቃቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply