የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ ጊዜ መመረጣቸው ይፋ ከሆነ በኃላ ሀገራት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የሩሲያ መንግሥት አስታወቀ

ቻይና፣ ሰሜን ኮርያ እና ቬንዙዌላ የመሳሰሉት ሀገራት የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የሩሲያ መንግሥት የዜና ምንጭ ታስ ዘገበ።

የሩሲያ ምርጫ ቦርድ ዛሬ እንዳስታወቀው ፑቲን ከ 87 በመቶ በላይ የመራጭ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል።

በዚህ መሠረት የ71 ዓመቱ ፑቲን ቢያንስ ለስድስት ዓመታት የስልጣን መንበሩን ይቆጣጠራሉ።

ገለልተኛ ታዛቢዎች እንደሚሉት የፕሬዚዳንቱ የምርጫ ውጤት የተገኘው በከፍተኛ አፈና፣ በማስገደድ እና በማጭበርበር እንደሆነ ነው።

የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ለፑቲን እንደ 2018ቱ ምርጫ የእንኳን ደስ ያልዎ መልዕክት እንደማያስተላልፉላቸው ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል ።

ይልቁንስ በዛሬዋ ዕለት ለሩሲያ ነፃነት እና ዲሞክራሲ የሚታገለውን የሩሲያ ህዝብ ያስባሉ ተብሏል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈፀመች በኋላ በርካታ ሀገራት ጀርባቸውን ሰጥተዋታል።

መጋቢት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply