የሪል ስቴት ተቋማት የተጋነነ ቃል መግባት ዘርፉን ተአማኒነት እያሳጣው ነው ተባለ

በተጋነነ ሆኔታ ቃል መግባት የሪልስቴት ዘርፉን ተአማኒነት እያሳጣው እንደሚገኝ የሪልስቴት ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ ለሚሰማሩ አካላት የሚሰጠዉ ፍቃድ ሌላኛዉ ችግር መሆኑንም ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉ የኪውቢክ ኢንጅነሪንግ፤ሴንቼሪ አዲስ ሪልስቴት፤አያት አክሲዮን ማህበርና ሜትሮፖሎታን ሪልስቴት አመራሮች ገልፀዋል፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች እና በመገናኛ ብዘኋን በግንባታ ላይ ያሉ ወይም ያለቁ ቤቶችን በቅናሽ ዋጋ ፤በረጅም ጊዜ የሚከፍሉት ፤የሚሉ ማስታወቂያዎችን በስፋት እንመለከታለን፡፡

ታዲያ ቤቶችን ቃል በገቡት መሰረት ገንብተው የሚያስረከቡ የሪልስቴት አልሚ ድርጅቶች እንዳሉ ሁሉ፤ያልገነቡትን ቤት ፤እንደገነቡ በማስመሰል ለቃላቸዉ ታማኝ ያልሆኑ የሪልስቴት አልሚ ድርጅቶች እንዳሉ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡

ከዚህም የተነሳ በሚዲናዋ የሪልስቴት ድርጅቱ ባለው ጊዜ ቤቱን አላስረከበኝም ፤ወይም ተጭበርበሪያለው በሚል የሚካሰሱ እና መፍትሄ ያላገኙ ግለሰቦች እንዳሉ አንስተዋል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉ የሪልስቴት አልሚ ድርጅቶችም አሁን ላይ ስራችንን እያበላሸ ና ችግር እየፈጠረብን ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም ማህበረሰቡ በማስታወቂያዎች ተታሎ ገንዘብ ከማውጣቱ በፊት ፤የሪልስቴቶችን ጀርባ ሊያጠና እንደሚገባ አነስተዋል፡፡

መንግስትም የሪልስቴት አልሚ ደርጅት ነኝ ብሎ ለመጣ ሁሉ ፍቃድ ከመስጠቱ በፊት ፤ጀርባውን ሊያጣራ እና ገንብቶ ለህዝብ የማቅረብ አቅሙን ሊፈትሽ እንደሚገባው አንስተዋል፡፡

ይህም ዛሬ ላይ በተለያዩ ምክኒያቶች ተአማኒነተን እያጡ ለመጡ የሪሊልስቴት ድርጅቶች ትልቅ መፍትሄን ያመጣል ብለዋል፡፡

በመሳይ ገብረ መድህን

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply