የሪያል ማድሪድ  የደጋፊዎች  የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ሆነ:: 

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም የሪያል ማድሪድ የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ጁድ ቤሊንግሀም ሎስ ብላንኮዎቹ የላሊጋ ፣ ሻምፒየንስ ሊግ እና ስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ሲያሳኩ ሀያ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ለቡድኑ ጥሩ የሚባል ግልጋሎት መስጠት ችሏል።

” በመጀመሪያ አመቴ ይህንን ሽልማት በማሸነፌ ኩራት ተሰምቶኛል የመረጡኝን ደጋፊዎች ሁሉ አመሰግናለሁ።”ሲል ቤሊንግሀም ከሽልማቱ በኋላ ተናግሯል።

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply