የሪፖብሊካን ጠቅላላ ጉባኤ በትራምፕ ንግግር ተጠናቀቀ

https://gdb.voanews.com/ECD72C09-260E-415F-8BAB-4EDEE5FC19F7_cx0_cy4_cw0_w800_h450.jpg

ፕሬዚዳንት ትረምፕ፣ በትናንትናው ምሽት በዋይት ሀውስ በስተደቡብ ባለው መስክ ላይ በተሰበሰቡ 1ሺ 500 ሰዎች ፊት ሆነው ባሰሙትን ንግግር፣ የመጨረሻውን የሪፖብሊካን ጠቅላላ ጉባኤ ዘግተዋል፡፡

በትናንቱ የሀሙስ ምሽት ንግግራቸው ፕሬዚዳንት ትረምፕ ከዚህ በፊት በ2016ቱ ጠቅላላ ጉባኤ እና በ2017ቱ በዓለ ሲመታቸው ላይ ያሰሟቸውን ፍሬ ነገሮች ነው መልሰው ያስታገቡት፡፡ እንዲህ አሉ

“ይህ ምርጫ የአሜሪካን ህልም የምናቆይበት ወይም ለሶሾሊስት አጀንዳ አሳልፈን ሰጥተን የተባረክንበትን እድላችንን የምናጠፋበት መሆኑን ይወስናል፡፡”

ቀደም ሲል አዋቂዎች እትህትማማቾች ያሰሙትን ንግግር ተከትለው ኢንቫካ ትረምፕ አባታቸውን አስተዋውቀዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል

“በዛሬው ምሽት እንደ ኩሩ የህዝብ ፕሬዚዳንት ልጅ ሆኜ፣ በፊታችሁ ቆሜያለሁ”

ሃገሪቱ በየጎዳናው በሚታዩ ነውጦችና ማኅበራዊ አለመረጋጋቶች ባተሞላችበት በአሁኑ ሰዓት ፕሬዚዳንት ትረምፕ ህግ እና ሥርዓትን አስፈላጊነት አስረግጠው የተናገሩ ሲሆን ጆ ባይደን ግን እንደ ሰጋር በቅሎ ማንም ግራ ክንፍ የዲሞክራቲክ ፓርቲ አክራሪ ሚጋልባቸው ናቸው በማለት ሊስሏቸው ሞክረዋል፡፡ እንዲህ አሉ

“ጆ ባይደን ደካማ ነው፡፡ ትዕዛዝ የሚቀበለው ከተማቸውን አውድመው ከወደመቸው ከተማ ደግሞ ከሚሸሹ ግብዞች ነው፡፡”

ሁለቱም የዴሞክራቲክ እና የሪፖብሊካን ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤዎች በግለሰብ ሰብዕና ያተኮሩ በመሆን ተተችተዋል፡፡ እጩዎቻችውን አግዝፈው ወይም ተቃዋሚዎቻቸውን አርክሰው ከመታየት ውጭ በፖሊሲ ጉዳዮች ዙሪያ በበቂ ሁኔታ ያሉት ነገር የለም፡፡ በቺካጎ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፈሰር ዊልያም ሆዌል፣ እንዲህ ይላሉ

“ያ በተለይ የሪፖብሊካን ፓርቲን ጠቅላላ ጉባኤ ሳስበው ትክክል የሚስለኛል፡፡ እሳክሁን ፕሬዚዳንት ትረምፕ ሊሰሩባቸው የሚፈልጓቸው ጉዳዮች ምን እንደሆኑ አልተገለጸም፡፡ በአንድ ወቅት ኢኮኖሚውን በጣም ያሳደግ ነውን ኢኮኖሚ አሁንም መልሰን እናመጣዋለን ከሚል ባዶ የተስፋ ቃል ውጭ የተገለጸ ነገር የለም፡፡ ካለንበት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝም እንዴት አድርገን እንደምንወጣ ተብራርቶ የተገለጸ ነገር የለም፡፡”

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አስመልክቶ ለሚያከናውኑት ሥራ ድጋፍ የሰጡት አሜሪካውያን ከአንድ ሦስተኛው እጅ ያነሱ ናቸው፡፡ በዚህ ዙሪያ የሚደርሱባቸውን ትችቶች የተከላከሉት አብዛኞቹ የአፍና አፍንጫ ጭምብል ሳያደርጉ ተጠጋግተው በተቀመጡ 1ሺ 500 ሰዎች ፊት ቆመው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ አብዛኞቹም የኮቪድ ምርመራ አልተደረገላቸውም፡፡

የትረምፕ ንግግር የሪፖብሊካንን ጠቅላላ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ያመለከተ ነው፡፡ ንግግሩ ከልማድና የስነሥርዓት ወግ ውጭ ባልተለመለደ መልኩ የተከናወነ ነው፡፡ አንዳንዶቹም ከዋይት ሃውስ በመካሄዳቸው በምርጫ ፉክክር መሳተፍና የመንግሥት አስተዳደር ኃላፊነት ወሰንን በመቀላቀል የሥነምግባር ህጉ የተጣሰባቸው መሆኑን እያነሱ የሚተቹም አሉ፡፡ 

ጉባኤው ያተኮረው የትረምፕ ጠንካራ የድጋፍ መሠረት የሆኑትና እንዲሁም በሴቶችና በቁጥር አንስተኛ የሚሆኑንን የማኅብረሰብ ክፍሎች ላይ ነው፡፡ በአደንዛዥ ዕጽ ሳቢያ የዕድሜ ይፍታህ ተፈርዶባት የነበረችውን ጥቁሯን አሊሳ ጆንስን ጨምሮ ባለቤቷ በህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት ሥራ ላይ እንዳለ የተገደለው የቀድሞ ጥቁር ፖሊስ መኮንን አን ዶርን የመሳሰሉትም የጉባኤው ተናጋሪዎች የነበሩት ለዚህ ነው፡፡ የሪፖብሊካን ስትራቴጂስት አማንዳ ኦቪኖ እንዲህ እንዲህ ይገልጹታል

“የወንጀል ህጉ ማሻሻያ የሰውን ህይወት የሚነካ መሆኑን ለማሳየት የአሊስ ጆንሰን ንግግር ተሰምቷል፡፡ “ምሽቱ ልብን የሚነካው የአን ዶርን ንግግር ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሁልጊዜ ህግና ሥርዓትን የማስፈንን አስፈላጊነት ለመሰበክ ስሜት ነኪ ነገሮችን ወደፊት ማምጣት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ እሷ ግን በትክክል ያንን መልዕክት ያደረሰች ይመስለኛል፡፡ በተለይም መልዕክቱ እንዲደርሳቸው ለሚያስፈልገው በመለስተኛ ከተሞች የሚኖሩ መራጮች ዘንድ ማለት ነው፡፡” 

ትረምፕ ንግግራቸው በሚያሰሙበት ወቅት ከዋይት ሃውስ ውጭ ተቃዋሚዎች ደግሞ ተቃውሞቸውን እያሰሙ ነበር፡፡ ይህ አገሪቱ ምን ያህል ጫፍና ጫፍ ይዛ እንደተከፋፈለችና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ወደ መጭው የጥቅምት ወር ምርጫ እያመራች መሆኑን ያሳያል። ዘገባውን የተከታተለችው በዋይት ሀውስ የቪ ኦ ኤ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳስኩዋራ ናት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply