የራያ ቆቦ ወረዳ በትግራይ ወራሪ ቡድን ስር ከወደቀበት እለት ጀምሮ ጠላት በህዝባችን ላይ አሰቃቂ የሆነ ድርጊት እየፈጸመ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 25 ቀን 201…

የራያ ቆቦ ወረዳ በትግራይ ወራሪ ቡድን ስር ከወደቀበት እለት ጀምሮ ጠላት በህዝባችን ላይ አሰቃቂ የሆነ ድርጊት እየፈጸመ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የትግራይ ወራሪ ሃይል የጭካኔ በትር በራያ ቆቦ ወረዳና ቆቦ ከተማ ላይ ጠላት ወደ አካባቢው ከገባበት እለት ጀምሮ እየተባባሰ መምጣቱን ከስፍራው የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የህወሃት መራሹ ቡድን በራያ ቆቦ የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ግድያ፣ አስገድዶ የመድፈር እና የዘረፋ ተግባሩን ቀጥሎበታል ተብሏል። በየግንባሩም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ የአማራ ፋኖ፣ የወረዳው ሚሊሻ እና አመራሩ በቅንጅት ተጋድሎ እየፈጸሙ ስለመሆኑ ተገልጧል። በሌላ በኩል ደግሞ ከራያ ቆቦ ተፈናቅለው በተለያዩ ከተሞች ለሚገኙ ሴቶች እና ህጻናት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲደረግላቸው ጥሪ እናቀርባለን ሲል የዘገበው የራያ ቆቦ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply