የራያ አላማጣን የመብራት ሃይል ስቴሽን ሲጠብቁ ከነበሩትና በጁንታው ጥቃት ደርሶባቸው በህይወት የተረፉት 16 የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ከሰባት ቀናት የእግር ጉዞ በኋላ ወልድያ ከተማ ገ…

የራያ አላማጣን የመብራት ሃይል ስቴሽን ሲጠብቁ ከነበሩትና በጁንታው ጥቃት ደርሶባቸው በህይወት የተረፉት 16 የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ከሰባት ቀናት የእግር ጉዞ በኋላ ወልድያ ከተማ ገቡ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሰሜን ዳይሬክቶሬት 4ኛ ዲቪዥን፣4ኛ ሻለቃ ምክትል ሻለቃ የሆኑት ረ/ኢ/ር አያልነህ ታረቀኝ የህብረተሰቡን ንብረት ሲጠብቁ በነበሩት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ የተሰነዘረውን እጅግ አሳፋሪ ጥቃት አምልጠው የመጡ 13 ወንዶችና 3 ሴቶች በአማራ ልዩ ሃይልና በሰሜን ወሎ ዞን የፀጥታ አመራሮች ጥረት ከጥቃት ተርፈው አሁን ተቀብለናቸዋል ብለዋል፡፡ ህዝባዊነትን ተላብሰው የህብረተሰቡን ንብረት ሲጠብቁ በነበሩ አባሎች ላይ የተቃጣው ድርጊት ኢሰብአዊ እና የባንዳነት ተገባር ነው ሲሉም ኮንነውታል፡፡ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የሰሜን ዲቪዥን 3 ሻለቃ አባላት የአላማጣን የመብራት ሃይል ስቴሽን እንደወትሮአቸው በመጠበቅ ላይ ነበሩ፡፡ በርካታ የታጠቁ የትግራይ ክልል ልዩ ሀይልና ሚሊሻ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ጥቃት ሰንዝረዋል አባሎቹም ከፍተኛ መከላከል ቢያደርጉም ሊቋቋሟቸው አልቻሉም ብለዋል፡፡ ግቢውን ጥሰው በመግባት አባላቱን በብሄር በማከፋፈልም ከፍተኛ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የሚፈልጓቸውን አባሎችን ይዘው መሄዳቸውን ረ/ኢ/ር አያልነህ ታረቀኝ ገልፀዋል፡፡ በካምፕ ውስጥ የሚፈልጉትን ትጥቅና ንብረቶችንም ዘርፈዋል ብለዋል፡፡ ኢትዮ አማራ ቱዩብ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply