የራያ አማራ አስመላሺ ኮሚቴ ውይይት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል! ~~~~~~ አሸናፊ ገናን ~~~~~~ የራያ አማራ የደረሰበት ማህበራዊ ሲቃ ከባድ ነው።የራያ ህዝብ… በማንነቱ የደረሰበት…

የራያ አማራ አስመላሺ ኮሚቴ ውይይት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል! ~~~~~~ አሸናፊ ገናን ~~~~~~ የራያ አማራ የደረሰበት ማህበራዊ ሲቃ ከባድ ነው።የራያ ህዝብ… በማንነቱ የደረሰበት ሰው ሰራሺ ጥቃት ቀላል አይደለም። ስለሆነም በራያ ህዝብ ጉዳይ መላው የአማራ ህዝብ በትኩረት ሊሳተፍ ይገባል። ለጥቂቶች ብቻ የሚሰጥ ነገር የለም።ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል። የህዝባችን አጠቃላይ ችግሮች በጋራ የሚፈቱ እንጅ ተራ በተራ የሚቀለበስ አይደለም። ስለሆነም የራያ አማራ አስመላሺ ኮሚቴ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በጣም የሚደነቅ ተግባር ነው። በምክክር መድረኩ ላይ የምስራቅ አማራ ፋኖዎች መገኘታቸውም ይበል የሚያሰኝ ነው። ስለዚህ የራያ አማራ ማህበራዊ ችግር የሁሉም አማራ ማህበራዊ ችግር መሆኑን ተገንዝበን። የአስመላሺ ኮሚቴውን እንቅስቃሴ በፅናት ልንደግፈው ይገባል። ማንነት እና ርስት በተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚፈታ ችግር የለም። የአማራ ፓለቲካ ውስብስብ ችግሮችን በመልክ በመልካቸው ለመፍታት ከፍተኛ የድ ፕሎማቲክ ስራዎችን መስራት አዋጭ ነው። የራያ ህዝብ በከፍተኛ ማህበራዊ ችግር ውስጥ እየኖረ መሆኑ ይታወቃል። አካባቢው አሁንም በጠላት ቁጥጥር ውስጥ መሆኑም ተጨማሪ ችግር ነው። በተለይም ከድጋሜው ጦርነት በኋላ የራያ አማራ ጭፍጨፋ እና ሰብአዊ ጭቆና ከባድ መሆኑም የሚታመን ነው። አሁንም በቅርብ ጊዜ አካባቢው ነፃ እንዲወጣ ጭምር መስራትን ይጠይቃል። የራያ አማራ ህዝብ አሁንም በጠላት እየተደበደበ መሆኑ በግልፅ የሚታወቅ ስለሆነ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ አካባቢውን ከትርምስ ሊያወጣው ይገባል። የራያ አማራ አስመላሺ ኮሚቴውም ለህዝባችሁ እየከፈላችሁ ያለው መስዋአትነት ታሪክም የሚረሳው አይደለም። በሁሉም አካባቢዎች ያለውን አላስፈላጊ መጓተት በጊዜ ለመፍታት የተጠናከረ ትብብር እና ስምምነትን ማካሄድ ያስፈልጋል። በዛሬው ዕለት የተደረገው ውይይት በሁሉም አካባቢዎች የጋራ ግንዛቤ እንዲሆኑ አዳድስ አሰራሮችን መዘየድ ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው። በዛሬው የውይይት መድረክ ብዙ ተግባራት መፈፀማቸው ደስ ይላል። ወደ ፊቱም መላውን አማራ ያሳተፈ ውይይት እንደምታዘጋጁ እተማመናለሁ። ሁሉም የአማራ ልሂቃን በራያ እና ወልቃይት ጉዳይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና የትብብር ስራ እንድሰራ ኮሚቴው በሃላፊነት ቢሰራ መልካም ነው ብየ አስባለሁ። ራያ አማራ ነው። ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 01/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply